( ኅዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም)
በየዓመቱ ኅዳር 8 ቀን የሚከበረው የአርባዕቱ እንስሳ የንግሥ በዓል በዛሬው ዕለት በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ ሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ሲራክ አድማሱ (የካቴድራላችን ዋና አስተዳዳሪ)፣ መልአከ ሰላም አባ ወልደ ኢየሱስ፣ ሊቃውንተ ቤ/ክ፣ የሰንበት ት/ቤታችን መዘምራን እንዲሁም በርካታ ምእመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።
በበዓሉ ላይም በሊቃውንተ ቤ/ክ (ፍቁራኒሁ ለአብ) እና በሰንበት ት/ቤታችን መዘምራን (ሱራፌል በግርማሆሙ) በየተራ ወረብ የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም የካቴድራላችን እድሳት የሚገኝበትን ደረጃ በተመለከተ አጭር ሪፖርት እንዲሁም በመምህር ኤፍሬም በየነ ለበዓሉ የሚስማማ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን በመጨመረሻም በሊቀ ስልጣናት ቃለ ምእዳን እና ቡራኬ በመስጠት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።