በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከብሮ ዋለ።

++++++++++++++++++++++++++++++++++

ጥር 7 ቀን 2014 ዓ/ም

(አዲስ አበባ: ኢትዮጵያ)

የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፥ ሊቃውንተ ቤተ ክስርስቲያንና በርካታ ምእመናን በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በዓውደ ምሕረት መርሐ ግብሩ “ዮም መላእክት ይዬብቡ ወሊቃነ መላእክት ይዜምሩ፤ እስመ መድኅን መጽአ ውስተ ዓለም ለቢሶ ሥጋነ”የሚል ያሬዳዊ ወረብ በሊቃውንት ሲቀርብ፤ በካቴድራሉ ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን ወይቤላ አብ ለማርያም አምጣንየ አምጣነኪ አዝማንየ አዝማነኪ ማርያም ድንግል ፥ ማርያም ሐቀፍኪዮ ወአመ ወለድኪ ” የሚል ያሬዳዊ ዝማሬ ተዘምሯል።

በመቀጠልም ያካቴድራሉ አስተዳዳሪ ሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ሲራክ አድማሱ ስለ ካትድራሉ ሪፖርት አቅርበዋል። ካቴድራሉ በአጼ ኃይለ ሥላሴ አማካኝነት በ1924 ዓ/ም ተመሥርቶ ግንባታው በ1936 ዓ/ም ተጀምሮ በ1939 ዓ/ም ተጠናቅቆ እስካሁን አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ገልጻል።

አሁን ግን ካቴድራሉ የማርጀትና የመሰንጠቅ አደጋ ስላጋጠመው ኮሚቴ ተዋቅሮ በባለሙያ ጥናት መሠረት ዕድሳት እንደሚያስፈልገው ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን አብራርተዋል።

በጥናቱ መሠረት የካቴድራሉ ሕንጻና መላ ግቢው ለማደስ ከ80 እስከ 100 ሚልዮን ብር እንደሚያስፈልግ በመግለጽ በውስጥም በውጭም የሚገኙ ምእመናን ለዕድሳቱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ከዚህ በመነሣት በዕለቱ የገቢ ማሰባሰብ መርሐ ግብር ተካሂዶ በርካታ ምእመናን በቀጥታ በመስጠትና ቃል በመግባት ተሳትፎ አድርገዋል፡፡

የካቴድራሉ ዋና ጸሐፊ ላእከ ሰላም ሽታው ብርሃኑ የካቴድራሉ ካህናት አገልጋዮችና የካቴድራሉ ልዩ ልዩ ሠራተኞች ለዕድሳቱ የሚውል የወር ደመወዛቸው መስጠታቸውን ገልጸዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ኤልያስ “ሠለስቱ ስም አሐዱ እግዚአብሔር” በሚል መነሻነት ቅድስት ሥላሴን በተመለከተ ሰፉ ያለ ትምህርት በመስጠት ቃለ ምዕዳንና አባታዊ መልአክታቸውን አስተላልፈዋል።

ታቦተ ሕጉም የካቴድራሉ ሕንጻ እስኪጠናቀቅ ድረስ ወደ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ገብቷል።

በበዓሉ ሊቃነ ጳጳሳት፥ በርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና አንደሰማይ ከዋክብት ደምቀውና አምረው የሚታዩ እጅግ በርካታ የተዋሕዶ ልጆች ምእመናንና ምእመናት ተገኝተዋል።።

ለካቴድራሉ ዕድሳት አስተዋጽኦ ማድረግ ለምትፈልጉ ሁሉ ከታች ባሉ የሒሳብ ቁጥር ማስገባት እንደምትችሉ ልንገልጽላችሁ እንወዳለን፦

1. 10000037786334 የኢ/ያ ንግድ ባንክ።

2. 53431186 አቢሲንያ ባንክ።

3. 7000022335516 ንብ ባንክ።

4. 01320414050300 አዋሽ ባንክ።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: Pre-qualification of Companies for the Renovation Works of Holy Trinity Church in Addis Ababa, Ethiopia Link to: Pre-qualification of Companies for the Renovation Works of Holy Trinity Church in Addis Ababa, Ethiopia Pre-qualification of Companies for the Renovation Works of Holy Trinity Church... Link to: የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተነ እንሠራለን መጽሐፈ ነህምያ ምዕ 2፡20 Link to: የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተነ እንሠራለን መጽሐፈ ነህምያ ምዕ 2፡20 የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top