በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

“ዋዋጎ” ቱውፊታዊ ድራማ ተመርቆ ለምእመናን እይታ ክፍት ሆኗል፡፡

July 7, 2023

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እድሳት ገንዘብ ማሰባሰቢ ያሚሆን በሊቀጉበኤ ታረቀኝ ብርሃኑ ተደርሶ በመርሐዬ ተውኔት ጥላሁን ዘውገ እና በታዋቂ አርቲስቶች የተተወነ “ዋዋጎ” የተሰኘ መንፈሳዊ እና ቱውፊታዊ ቲያትር ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የበላይ ጠባቂ፣ የተለያዩ አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ማኅበረ ካህናት እና ምእመናን በተገኙበት ቅዳሜ ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ/ም በቡራኬ ተመርቆ ለምእመናን እይታ ክፍት ሆኗል፡፡

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳደር እና ሰበካ ጉባኤው በቃለ አዋዲው ደንብና ሕግ መሠረት እራሱን የቻለ የሕንፃ ዕድሳት አሠሪ ዐቢይ ኮሚቴ በማዋቀር ልዩ ልዩ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ቆይቶ በቅርስ ጥገና ሥራ ላይ ሙያ ያላቸውን መሐንዲሶችን በማሳተፍ እንዲሁም በሀገሪቱ ካለው የቅርስ ጥበቃ ባለ ሥልጣን መ/ቤት ጋር ምክክር በማድረግ የካቴድራሉ ሕንፃ በከፍተኛ ደረጃ ዕድሳት እየተደረገለት ይገኛል፡፡ ለካቴድራሉ ዕድሳት ሙሉ ገቢ የሚሆን “ዋዋጎ” የተሰኘ የአብነት ትምህርት ቤቶች እና የቅኔ ትምህርት ቤቶች ለቤተክርስትያን ያላቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላይ ያጠነጠነ እንዲሁም የገጠሪቷን ቤተክርስትያን ችግር አጉልቶ የሚያሳይ ድንቅ መንፈሳዊ ድራማ ከአርቲስቶች ጋር በመተባበበር በመታየት ላይ ይገኛል፡፡ በትዕይንቱ እየተማሩ የቅድስት ሥላሴ ካቴድራልን ሕንፃ እድሳት ይደግፉ፡፡

ቲያትሩ ቅዳሜ ሐምሌ 1 ፣ 15 እና 22 ቀን 2015 ዓ/ም በካቴድራሉ ሁለገብ አዳራሽ ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ ከተለያዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች ጋር ይቀርብላችኃል፡፡ የመግቢያ ትኬቱን በዕለቱ የሚገኙ ሲሆን ዋጋውም 200.00ብር እና 300.00 ብር መሆኑንን አዘጋጅ ኮሚቴው ገልጸል፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/htc.org_.et-cover.jpg 400 400 tc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png tc2023-07-07 09:46:522023-07-07 09:51:26“ዋዋጎ” ቱውፊታዊ ድራማ ተመርቆ ለምእመናን እይታ ክፍት ሆኗል፡፡

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: “ዋዋጎ” ቱውፊታዊ ድራማ Link to: “ዋዋጎ” ቱውፊታዊ ድራማ “ዋዋጎ” ቱውፊታዊ ድራማ Link to: በከፍተኛ ጥራት እና ፍጥነት ሁለንተናዊ ዕድሳት እየተከናወነለት የሚገኘው የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል እድሳት ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ የሚያሳዩ ምስሎች – መስከረም 2016 ዓ.ም Link to: በከፍተኛ ጥራት እና ፍጥነት ሁለንተናዊ ዕድሳት እየተከናወነለት የሚገኘው የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል እድሳት ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ የሚያሳዩ ምስሎች – መስከረም 2016 ዓ.ም በከፍተኛ ጥራት እና ፍጥነት ሁለንተናዊ ዕድሳት...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top