ሁለንተናዊ ዕድሳት እየተከናወነለት የሚገኘው የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ከእድሳት ሥራዎቹ መካከል የጉልላት እና በጉልላቱ ላይ የሚቀመጠው መስቀል እድሳት ሥራ ተጠናቋል፡፡
“እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገልን፥ ደስም አለን።” (መዝሙር 126፥3)
በእድሳት ላይ የሚገኘው ታላቁ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሕንጻ ቤተክርስቲያን በእድሳት ምክንያት ወርዶ የነበረው የቤተክርስቲያን ዓርማ መስቀሉ በዕለተ ተቀጸል ፅጌ በዓለ መስቀል ክብረ በዓል ዕለት ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ከየአድባራቱና ገዳማቱ የመጡ ማሕበረ ካህናት እንዲሁም ማህበረ ምእመናኑ በተገኙበት ጉልላተ መስቀል የማኖር ሥነስርዓት በጸሎት እና በያሬዳዊ ዝማሬ በብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ በታላቅ ድምቀት ይከናወናል ። እነሆ የቤተክርስቲያን ልጆች የሆናችሁ ምዕመናንም የዚህ ደስታና በረከት ተካፋይ እንድትሆኑ በሥላሴ ስም ጥያችንን እናስተላልፋለን። በአካል መገኘት የማትችሉ በካቴድራሉ ይፋዊ ዩቲዩብ ቻናል (ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አ/አ (HTC)) መስከረም 10 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ይከታተሉ፡፡