ለካቴድራሉ እድሳት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር (በመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል/4 ኪሎ)
“አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም።”
— ኤርምያስ 32፥17
እነሆ ታላቁ እና ታሪካዊው የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እድሳት በሥላሴ አጋዥነት ከታሰበው በላይ በፍጥነት በመከናወን ላይ ይገኛል ። ለዚህም ቅድስት ቤተክርስቲያን በሥላሴ ስም ለልጆቿ ምሥጋናዋን ታቀርባለች ።
እንደ ከዚህ ቀደሙ እናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለማደስ እንደተጋን አሁንም ድጋፋችሁን በማድረግ እድሳቱ ተጠናቆ የ ቃልኪዳኑ ታቦት ወደ መንበረክብሩ በክብር እንዲመለስ ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ።
እለት እለት የምንናፍቀውን ጥር እና ሀምሌ የአጋእዝተ አለም ሥላሴ ንዑድ እለት ለማየት ይረዳን ዘንድ እሑድ ታህሳስ 21ቀን ከቀኑ በ7:30 ሰዓት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለወልድ ሁለገብ አዳራሽ ውስጥ በሚደረገው የ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር ላይ እንዲገኙ በክብር ጠርተንዎታል::
በረከተ ሥላሴ በሁላችን ላይ ይደር