“ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
በቀደሙት አባቶቻችን ጥረት እና ተጋድሎ የቆዩልንንና አገራችን በዓለም መድረክ ጎልታ እንድትታወቅ ያደረጉ ቅርሶቻችንን ትላንት በነበሩበት ውበትና ለዛ ልንጠብቃቸውና ልንከባከባቸው ይገባል፡፡ ከእነዚህ ቅርሶቻችን መካከል አንዱ ደግሞ በከተማችን አዲስ አበባ የሚገኘው የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ነው:፡ ይህ ታላቅ ካቴድራል አሁን ላይ እድሳት እየተደረገለትና እድሳቱም በመጠናቀቅ ላይ ስለሆነ ከበረከቱና ከታሪኩ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ባሉበት ሆነው የሚረዱበት የቀጥታ ገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር የፊታችን ዓርብ ሰኔ 7 ከቀኑ 12:00 ጀምሮ በታላቅ ድምቀት ይከፈታል።
ይህም መርሐ ግብር ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሰኔ 7፣8 እና 9 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በካቴድራሉ ሚዲያ፣በራማ ቲዩብ ፣በቋንቋዬነሽ ሚዲያ፣በነጋሽ ሚዲያ፣በመንክር ሚዲያ፣በ21 ሚዲያ፣ በንቁ ሚዲያ እንዲሁም በተለያዩ የዩቲዩብና የቴሌቭዥን ቻናሎች ይተላለፋል።በተጨማሪም በተመረጡ የቲክቶክ ገጾች እና ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፍ ይሆናል። በረከቱ እንዳያመልጥዎ በዕለቱና በሰአቱ ዝግጁ ይሁኑ፡፡