የሁለትዮሽ ውይይት ከኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር
የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ካቴድራሉን የቱሪስት መድረሻነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ይቻል ዘንድ የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን የካቴድራሉ የሰበካ ጉባዔ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ እንደ ጽ/ቤቱ መግለጫ አሰራሩን ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ ከአገር ገጽታ ግንባታ ላይ የበኩሉን ለመወጣት ያግዝ ዘንድ የካቴድራሉ ቱሪዝምና ቅርስ ጥበቃ ክፍል በአዲስ መልክ ኮሚቴዎች አቋቁሞ የአጭርና የረጅም ዕቅዶችን በማውጣት ስራውን በይፋ ጀምሯል፡፡
- በተያያዘ ዜና የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሙሉ ታሪክ የሚያሳይ DVD ከባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለካቴድራሉ ተበርክቷል፡፡
- በሌላ ዜና የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በአገር ግንባታ ሒደት ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ በኃይሌ ገብረሥላሴ ጐዳና በተለምዶ ሃያ ሁለት በሚባል አካባቢ በአርባ አምስት ሚሊዮን ብር ወጪ ዘመናዊ ሁለገብ ህንፃ እየገነባ መሆኑን የሰበካ ጉባዔ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
- በአሁኑ ወቅትም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በአዲስ መልክ ለማሠራት ፕላኑንና ዲዛይኑን ሁሉ አልቆ ከክፍለ ከተማ ፈቃድ እየተጠባበቀ መሆኑንና ሥራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመር ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡