ዓመታዊው የዓጋዓዝተ ዓለም ሥላሴ በዓል በድምቀት ተከበረ

በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

በየዓመቱ ሐምሌ 7 ቀን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሚከበረው ዓመታዊው  የሥላሴ በዓል በዚህ ዓመትም በመንበረ ጸባዖት ቅድሰት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኩሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንትና ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት እጅግ በጣም ደማቅ በሆነ ሁኔታ በዓሉ ተከብሮ ውልዋል፡፡

በዓሉ መከበር የጀመረው ከዋዜማው ከሐምሌ6 ጀምሮ ሲሆን የካቴድራሉ ካህናትና መዘምራን ከዋዜማው ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ለ24 ሰዓታት ያህል ሌሊትና ቀኑን ሙሉ ያለ ማቋረጥ ስብሃተ እግዚአብሔር ሲያቀርቡ ውለው አድረዋል፡፡

ይህመንፈሳዊ አገልግሎት ማለትም ስርዓተማህሌተ፣ ስርዓተቅዳሴ እንዲሁም ሰዓታትና ሰርክ ፀሎት በአጠቃለይ የስርዓተ አምልኮ አፈፃፀም በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ልዩ በመሆኑ የእምነቱ ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም እጀግ በጣም የሚስደንቅ በዓል ነው፡፡

በሌላ ዜና የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኩሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት 20ኛው በዓለ ሲመት ሐመሌ 5/11/04 ዓ.ም በካቴድራሉ በታላቅ ደምቀት ተከብሮ ውልዋል፡፡

 

በበዓሉ ላይ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ፣የመንግስት ተወካይ፣ የኦሬንታል ቤ/ክ ተወካዮች፣የአፍሪካ ቤ/ክ ዋናፀሐፊ የአ.አአ ዳባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ፀሐፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና እንዲሁም በብዙሽህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ በዓሉ ተከብሮ ውልዋል፡