በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለካቴደራሉ እድሳት የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተካሄደ
በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ
ቀደም ሲል የዘሁ ዓይነት መርሃ ግብር መጋቢት 10/2004 ዓ.ም ተካሂዶ የነበረ ሲሆን በድጋሚ በሳለፍነው ሳምንት ሰኔ 24/2004 ለሁለተኛ ጊዜ ተካሂዷል በዚሁ ዕለት እነ መሠረት መብራቴን ጨምሮ ታዋቂ አርቲስቶች የተገኙ ሲሆን ዕለቱን አስመልክቶ ያዘጋጁትን መዝሙር፣ ድራማና ግጥም ለታዳሚዎች ምእመናን አቅርበዋል አበረታች የሆነ ውጤትም ተገኝቷል በቀጣይም የዚህ ዓይነት መርሃ ግብር ሊዘጋጅ እንደሚችል የካቴድራሉ አስተዳደር ገልጿል፡፡
በሌላ ዜና የካቴድራሉ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ሰርቲፊኬት ሐምሌ 1/2004 ዓ.ም የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ በተገኙበት መርሃ ግብሩ ተካሂዷል፡፡ በዚሁ ዕለት ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎችና ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተማሪዎች በካቴድራሉ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ ሽልማት ተሰጧቸዋል፡፡