በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

በሃይማኖት ሽፋን ቅ/ኤልያስ መጥቷል ብለው በኤልያስ ስም ሲነግዱ የነበሩ ግለሰቦች ንፁሀን ዜጎችን ሲያስደበድቡና ሁከት ሲፈጥሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ታሰሩ

April 24, 2013

ቀደም ሲል በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በተለያዩ የቤተክርስቲያኒቷ አገልጋዮች የተፃፉትን ጽሑፎች በአህጉረ ስብከታችን ዌብ ሳይት ስናስነብብ መቆየታችን አይዘነጋም፡፡

ምንም እንኳን ጉዳዩ ዘግይቶ በተለያዩ ሚዲያዎች መሰራጨት የጀመረ ቢሆንም ቀደም ሲል ከሁለት ዓመታት በፊት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጀርባ በተለምዶ ቆሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው መንደር ቤተክርስቲያኑንና ህብረተሰቡን ሲረብሹ የቆዩ ሲሆን የካቴድራሉ ጽ/ቤት ጉዳዩን እየባሰ ሲሄድ በመስከረም ወር 2ዐዐ5 ዓ.ም ጉዳዩ በፍርድ ቤት እንዲታይ ክስ መስርቶ በፍ/ቤት ትእዛዝ ግለሰቦቹ ከተከራዩት ቤት እንዲወጡና አከራዮችም ተከራዮቹ በአስቸኳይ እንዲያስወጡ ውሳኔ ተወስኖ ነበር፡፡

ይሁንና ግን በአፈፃፀም ሂደት የሚመለከታቸው አካላት እስከ አሁን ድረስ እልባት ባለማግኘቱ ካቴድራሉንና በካቴድራሉ ጀርባ ያሉ ነዋሪዎች ከመጠን በላይ ሲቸገሩ ቆይተዋል፡፡ ግለሰቦቹ መኖሪያ ቤታቸው የት እንደሆነ በእርግጠኛነት ማወቅ ባይቻልም ሁሉም የሚገናኙት ከሥላሴ ጀርባ በተከራዩት ቤት ነው የመገናኛ ሰዓታቸውም ከቀኑ በ11 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6፡3ዐ ነው፡፡

የተከራዩት ቤት መጠኗ አነስተኛ ብትሆንም እስከ 4ዐዐ የሚደርሱ ሰዎች ኃይማኖትን ይሁን ፖለቲካ፣ እብደት ይሁን ስካር ባልታወቀ ሁኔታ ከበሮ እየመቱ እጣን እያጨሱና መጠጥ እየጠጡ እንደሚያመሹ የሰፈሩ ሰዎች በግልጽ ከመናገራቸውም በላይ ከቅዳሜ በስተቀር ሁልጊዜ እዛው ቦታ ላይ የሚሰበሰብ ሲሆን ከቤቱ ጎን ያሉ ነዋሪዎች ማለፍ አትችሉም፣ ጫማችሁን አውልቁ ወዘተ እያሉ በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን በሰላም የመኖር መብት ሲያሳጧቸው የቆዩ ከመሆናቸውም በላይ ይባስ ብሎ በ15/ዐ8/2ዐዐ5 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡3ዐ ላይ እንደ ሰፈሩ ሰዎች አባባል ቁጥራቸው ከ5ዐ – 1ዐዐ የሚሆኑ በሰፈሩ ሰዎች ላይ ለማድረስ ጀምረውት የነበረውን የድብደባ ጥቃት በአካባቢ ባሉት የፖሊስና የመከላከያ ኃይል አማካይነት ጉዳቱ ሊቀንስ ቢችልም በዚሁ ዕለት ጉዳዩን በዋናነት ሲመሩ የተገኙት (የነበሩት)እጅ ከፍንጅ ተይዘው 4 ኪሎ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ፡፡ ቦታው ድረስ በአካል ሄደን ለማረጋገጥ እንደቻልነው 3 ሰዎች ተመትተው እቤታቸው ተኝተው አይተናል፡፡

የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም ቦታው ድረስ በመሄድ በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ የሆነ ክትትል እያደረጉ ሲሆን የካቴድራሉ ጽ/ቤትም ከአሁን ቀደም ከቤቱ እንዲወጡ ፍ/ቤቱ የወሰነበትን ውሳኔ አያይዞ ለፖሊስ ጣቢያው ልኳል፡፡ የአካባቢው ማኀበረሰብም ፖሊስ ጣቢያው ድረስ በመሄድ ለዓመታት በዚሁ ችግር ሲኖሩ መቆየታቸውንና አሁን የደረሰባቸውን ችግር ገልፀው ክስ መስርተውባቸዋል፡፡

በመሆኑም የሚመለከታቸው የቤተክርስቲያኒቱ ባለድርሻ አካላት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የቤተክርስቲኒቷን ስም በማጥፋታቸው በህግ መጠየቅ ይገባቸዋል እንላለን፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png 0 0 tc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png tc2013-04-24 16:19:332013-04-24 16:19:33በሃይማኖት ሽፋን ቅ/ኤልያስ መጥቷል ብለው በኤልያስ ስም ሲነግዱ የነበሩ ግለሰቦች ንፁሀን ዜጎችን ሲያስደበድቡና ሁከት ሲፈጥሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ታሰሩ

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: “ተረፈ አይሁዳዊነት በኤልያሳዊነት ስም ሲበቅል” አዲስ ሃይማኖት Link to: “ተረፈ አይሁዳዊነት በኤልያሳዊነት ስም ሲበቅል” አዲስ ሃይማኖት “ተረፈ አይሁዳዊነት በኤልያሳዊነት ስም ሲበቅል”... Link to: በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ አረጋወያን ለ7ኛ ጊዜ እረዳታ ተሰጠ Link to: በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ አረጋወያን ለ7ኛ ጊዜ እረዳታ ተሰጠ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top