በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት የውሃ ማጣሪያ ማሽን ተገጥሞ ሥራ ላይ ዋለ

June 8, 2013

0001

የውሃ ማጣሪያ ማሽኑ እስፕላሽ ኢንተርናሽናል ከሚባል ግብረ ሰናይ ድርጅት በእርዳታ የተገኘ ሲሆን ለዚሁ ሥራ ከ120,000.00 ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሚሊዮን ገልጸዋል፡፡

ማሽኑ የተለያዩ ጀርሞችና ቆሻሻን በሚገባ ከመከላከሉም በላይ የምንጠጣው ውሃ ጥሩ ጣዕም እንዲኖረው እንደሚያደርግም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በዚሁ የምረቃ ፕሮግራም ላይ የተገኙት ክቡር ሊቀ ሥልጣናት አባ ገ/ሥላሴ የካቴድራሉ ዋና አስተዳዳሪ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልእክት እግዚአብሔር ውሃውን ንጹህ አድርጎ የፈጠረ ሲሆን ነገር ግን የሰው ልጅ በተለያየ ሰው ሰራሽ ነገሮች ውሃ እንደሚበከል ገልጸው ሆኖም ግን እግዚአብሔር ለሰው ልጅ በሰጠው ጸጋ ሳይንሱንና ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ይህንን የመሰለ የውሃ ማጣሪያ ተሰርቶ አገልግሎት ላይ በመዋሉ የሚያስደስት መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

በመሆኑም ማሽኑ በሰው ሰራሽ ነገሮች እንዳይበላሽ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግበት እንደሚገባ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ አያይዘውም ይህንን የመሰለ እርዳታ ላደገው ለእስፕላሽ ኢንተርናሽናል ድርጅትና ሃላፊዎች በካቴድራሉ ስም ከፍተኛ የሆነ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በቀጣይም በተለያዩ የመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ የድርጅቱ ትብብር እንደማይለያቸው እምነታው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከሊቀ ሥልጣናት በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የካቴድራሉ ዋና ፀሃፊ ክቡር ሊቀ ስዩማን ወንደወሰን ቱሉ ሲሆኑ የካቴድራሉ አስተዳደር ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሳይውልና ሳያድር ስራው እንዲሰራ ከመፍቀዱም በላይ በድርጅቱ በኩል የተጠየቀውን የተወሰነ ወጪ በካቴድራሉ ወጪ ተደርጎ በአስቸኳይ ሥራው እንዲሰራ በማድረግ ካቴድራሉ ከፍተኛ የሆነ የሥራ ትብብር ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

ከክቡር ዋና ፀሃፊው በመቀጠል ንግግር ያደረጉት ወ/ት ቤተልሔም የሴቭ ሄቨን ድርጅት የአገር ውስጥ ተጠሪ ናቸው ወ/ት ቤተልሔም እንደገለጹት በካቴድራሉ ት/ቤት 96 ተማሪዎችን ድርጅታቸው እየረዳቸው እንደሚያስተምሩ ገልጸው የውሃ ማጣሪያ ማሽን እርዳታ ያደረገው የድርጅት ኃላፊዎች ት/ቤቱን እንዲያዩት በመጋበዝ እርዳታው በእሳቸው ጋባዥነት ሊገኝ እንደቻለ ገልጸዋል፡፡ ንጹህ ውሃ ለሰው ልጅ ሊሰጠው የሚችለውን አገልግሎት በሰፊው አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም በክቡር ሊቀ ሥልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ የካቴድራሉ ዋና አስተዳዳሪ አማካኝነት የውሃ ማጣሪያ ማሽኑ ተባርኮና ተመርቆ የበአሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡

{flike}{plusone}

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/0001.jpg 480 640 tc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png tc2013-06-08 07:24:352013-06-08 07:24:35በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት የውሃ ማጣሪያ ማሽን ተገጥሞ ሥራ ላይ ዋለ

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: በዓላትን ማክበር ያለብን ያጡትንና የተቸገሩትን በማሰብ/በመርዳት መሆን እንዳለበት ተገለፀ Link to: በዓላትን ማክበር ያለብን ያጡትንና የተቸገሩትን በማሰብ/በመርዳት መሆን እንዳለበት ተገለፀ በዓላትን ማክበር ያለብን ያጡትንና የተቸገሩትን... Link to: የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ተጠናቀቀ Link to: የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ተጠናቀቀ የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top