በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

የብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የ1ኛ ዓመት መታሰቢያ የፀሎት ስነ ሥርዓት ተካሄደ

August 20, 2013

0021

ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ የተለዩት የ5ኛው ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝደንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ኅልፈት የአንደኛ ዓመት መታሰቢያ ሥነ ሥርዐት ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በማሕሌት፣ በጸሎተ ፍትሐትና በቅዳሴ ታስቦ ውሏል፡፡በመታሰቢያ ክብረ በዓሉ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፤ ካህናትና ምእመናን የተገኙ ሲሆን በቅዱስነታቸው መሪነት ሙሉ ፀሎተ ፍትሐት ከደረሰ በኋላ ከሰዓት ፀሎተ ቅዳሴው ተከናውኗል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በ20 ዓመት የፕትርክና ዘመናቸው ለሀገራቸውና ለዓለም ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደነበር በዚሁ የመታሰቢያ መርሃ ግብር ላይ ተገልጿል፡፡ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የአንደኛ ዓመት መታሰቢያ የፀሎት ስነ ሥርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ባለው መካነ መቃብራቸው ላይ ተካሂዷል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሐምሌ 1984 ዓ.ም ፓትሪያሪከ ሆነው ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ ለሀገር እድገትና ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት ለ20 ዓመታት ሐወርያዊ ተልእኳቸውን በመፈፀምና ከፍተኛ አገልግሎት በማበርከት ለቅድስት ቤተክርስትያንና ለሀገሪቱ ታላላቅ ሥራዎችን ሰርተው ማለፋቸው ተገልጿል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ በስነ ሥርዓቱ ላይ እንደገለፁት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ በህይወት ዘመናቸው ለትምህርት መስፋፋት፣ ለሀገርና ለዓለም ሰላም እንዲሁም የኃይማኖት መቻቻልንም በሰፊው በማስተማርና በቤተክርስትያኗ ለሀገር እድገት ጉልህ አስተዋፅኦ እንድታበረክት በማስቻል ከፍተኛውን ሚና ያበረከቱ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አንደኛ ዓመት መታሰቢያ ስነ ሥርዓት ነሐሴ 14/2005 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ባለው መካነ መቃብሩ ተካሂዷል፡፡በመታሰቢያ ክብረ በዓሉ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፤ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ሚኒስትሮች፤ ክብርት ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን ፤ ካህናትና ምእመናን በታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ መካነ መቃብር በፀሎቱ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በመታሰቢያ የፀሎት መርሐ ግብሩ ላይ ለተገኙ ምዕመናን ሠፊ የሆነ ትምህርተ ወንጌል ሠጥተዋል ፡፡

00020

{flike}{plusone}

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/0021.jpg 480 640 tc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png tc2013-08-20 16:08:492013-08-20 16:08:49የብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የ1ኛ ዓመት መታሰቢያ የፀሎት ስነ ሥርዓት ተካሄደ

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ ጾመ ፍልሰታን አስመልክተው ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን Link to: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ ጾመ ፍልሰታን አስመልክተው ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ ጾመ ፍልሰታን... Link to: ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሠራተኞች የቁጥጥርና የሥራ አመራር ሥልጠና ተሰጠ Link to: ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሠራተኞች የቁጥጥርና የሥራ አመራር ሥልጠና ተሰጠ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሠራተኞች የቁጥጥርና...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top