በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

የካቴድረሉ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

August 7, 2014

0022

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መልካም ፈቃድ ከነሐሴ 1 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም. ጀምሮ  የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ ሲሆኑ ሐሙስ ነሐሴ 1 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም. የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባዔ አባላት፣መላው ማህበረ ካህናት፣ መዘምራን፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና የአጥቢየው ምእመናን  ደማቅ አቀባበል አድርጐላቸዋል፡፡

ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ በካቴድራሉ ሲሾሙ አሁን ለ2ኛ ጊዜ ሲሆን ቀደም ሲል ከ2004 እስከ 2005 ዓ.ም ካቴድረሉን ባስተዳደሩበት ጊዜ ብዙ ሥራ እና መልካም አስተዳደር ከማስፈናቸውም በላይ ለካቴድራሉ መንፈሳዊ እና ለሁለንተናዊ አገለግሎት የሚሆን ብዙ ገንዘብና ጥሬ እቃ ካሰባሰቡ በኋላ በደብረ ገነት መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ማህበረ ካህናትና ማህበረ ምእመናን ጥያቄ አማካኝነት ለ1 ዓመት ያህል ወደ መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሄደው ዘርፈ ብዙ ልማት ካለሙ  በኋላ ልክ በ1 አመታቸው በካቴድራሉ ማህበረ ካህናት እና ልይ ልዩ ሠራተኞች ጥያቄና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መልካም ለ2ኛ ጊዜ የካቴድራሉ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመው መጥተዋል፡፡ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ ወደ ካቴድራሉ በድጋሚ እንዲመጡ የተመረጡበት መክንያት መንፈሳዊና የልማት አባት በመሆናቸው ሲሆን ከአሁን በፊት የሠሯቸው ሥራዎች ትላልቅ ማረጋገጫዎች ናቸው፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ የካቴድራሉ የበላይ ጠባቂና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ፤የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች  ፤የደብረ ገነት መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ካህናት፤የካቴድራሉ ማህበረ ካህናትና ልይ ልዩ ሠራተኞች በክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተዋል፡፡ በዓሉን አስመልክቶም የተለያዩ ቅኔዎችና ዝማሬዎች በካቴድራሉ ሊቃውነት  አማካኝነት ቀርቧል፡፡
በስተመጨረሻ የተደረገላቸውን አቀባበል በማስመልከት ንግግር ያደረጉት ክቡር ሊቀስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ ሲሆኑ የተደረገላቸውን አቀባበል ካመሰገኑ በኋላ ካቴድራሉ ዓለም አቀፋዊ እንደመሆኑ መጠን በልማትና በመልካም አስተዳደር ወደተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ የሁሉም ሠራተኛ እና ምእመናን አስተዋጽኦ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከዚሁ ጋር አያይዘውም ዘመኑ በሚፈቅደው አስተሳሰብና አሰራር ሰዎች መሥራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡ ሥርዓተ ቅዳሴው በክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ መሪነት ከተከናወነ በኋላ የበዓሉ ፍፃሜ ሆኗል፡፡
መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸውም ሁሉም የካቴድራሉ ሠራተኞች ተመኝተውላቸዋል፡፡

{flike}{plusone}

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/0022.jpg 480 640 tc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png tc2014-08-07 16:29:592014-08-07 16:29:59የካቴድረሉ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: ዓመታዊው የዓጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ክብረ በዓል በድምቀት ተከበረ Link to: ዓመታዊው የዓጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ክብረ በዓል በድምቀት ተከበረ ዓመታዊው የዓጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ክብረ በዓል... Link to: ለቅዱሳን ፓትርያርኮችና ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጸሎተ ፍትሐት ተደረገላቸው Link to: ለቅዱሳን ፓትርያርኮችና ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጸሎተ ፍትሐት ተደረገላቸው ለቅዱሳን ፓትርያርኮችና ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top