በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የአንድነት ጉባኤ መርሃ ግብር ተካሄደ

March 2, 2015

0005

የካቲት 14 እና 15 2007 ዓ.ም ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ  ልዕኮ ዋና ክፍል አስተባባሪነት የአንድነት ጉባኤው ተጀምሯል፡፡ በዚሁ የአንድነት ጉባኤ መርሃ ግብር ላይ የተለያዩ መምህራን ወቅቱን አስመልክተው ለምዕመናን ትምህርተ ወንጌል የሰጡ ሲሆን እንደዚሁም ወቅቱን የተመለከቱ የተለያዩ  መዝሙሮች በተለያዩ ዘማሪያን ቀርበዋል፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ዋና ክፍል አስተባባሪነት የተጀመረው ይህ የገዳማት እና   አድባራት የአንድነት ጉባዔ የተጀመረው የካቲት 14 ቀን 2007 ዓ.ም በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል  ሲሆን የዚሁ ዓይነት ጉባዔም በሁሉም የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ሊካሄድ እንደሚችል ታውቋል፡፡ የአንድነት ጉባዔው ምደባ  ከሶስት አድባራት እስከ አስር አድባራት የሚያጠቃልል  እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡
የዚህ ዓይነት የአንድነት ጉባኤ ቀደም ሲል ሲካሄድ የነበረ ቢሆንም ለተወሰነ ጊዜ የአንድነት ጉባዔው ተቋርጦ የነበረ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ ይሁን እንጂ የአንድነት ጉባዔው ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት፤ ምዕመናንን ወደ ንስሐ ለማቅረብና በሃይማኖታቸው ጸንተው እንዲኖሩ ለማድረግ የአንድነቱ ጉባኤ መቀጠል ጠቀሜታው እጅግ የጎላ በመሆኑ የክፍላተ ከተማ  የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊዎች እና የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ዋና ክፍል ባደረጉት የጋራ ምክክርና ውይይት ቀደም ሲል ተጀምሮ የነበረው የአንድነት ጉባዔ በማህበረ ካህናትም ሆነ በማህበረ ምዕመናን ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበረ መሆኑን በማውሳት ለወደፊቱም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል በማለት ስምምነት ላይ የተደረሰ በመሆኑ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትም በጉዳዩ ላይ ትኩረት በመስጠት ለሁሉም አድባራት ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት  የአንድነት ጉባዔው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን  ጾም ምክንያት በማድረግ ጉባዔው በሰባቱም ክፍላተ ከተሞች ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመደረግ ላይ ነው፡፡ የአንድነቱ ጉባዔ የሚካሄድባቸው ቀናት በየሳምንቱ ቅዳሜ እና እሁድ እየተከተለ ሲሆን በተለይም በርካታ ምዕመናን የሚገኙባቸውን ወርሃ በዓላት እና ዓመት በዓላትን ምክንያት በማድረግ ነው፡፡
 የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንዲሰጡ የሚጋበዙ መምህራነ ወንጌል በገዳማት  እና  አድባራት ጽ/ቤት ጠያቂነት ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ በየገዳማቱ  እና  አድባራቱ  ተመድበው የሚያገለግሉ ሰባክያነ ወንጌል እና በትሩፋት የሚያገለግሉ የወንጌል አገልጋዮች ናቸው፡፡ መነሻውን ከመንበረ ፀበኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያደረገው ይህ ዐቢይ የአንድነት ጉባኤ በተለያዩ ገዳማት  እና  አድባራት  የሚከናወን ሲሆን መጋቢት 26 እና 27/2007 ዓ.ም በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል፡፡

{flike}{plusone}

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/0005.jpg 480 640 tc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png tc2015-03-02 13:07:172015-03-02 13:07:17በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የአንድነት ጉባኤ መርሃ ግብር ተካሄደ

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: እንኳን ለአጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ አመታዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ Link to: እንኳን ለአጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ አመታዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ እንኳን ለአጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ አመታዊ... Link to: የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖ 2ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ተከበረ Link to: የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖ 2ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ተከበረ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top