የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሠራተኞች ልዩ የፅዳታ ዘመቻ አካሄዱ
የካቴድራሉ ልዩ ልዩ ሠራተኞች ጥቅምት 23/2009 ዓ.ም በካቴድራሉ ቅጥር ግቢ በዓይነቱ የተለየ የፅዳታ ዘመቻ በህብረት አካሂደዋል፡፡ይህ አባቢውን/ግቢውን የማጽዳት ሥራ ሲካሄድ ለ3ኛ ጊዜ ሲሆን 1ኛው እና 2ኛው የፅዳታ ዘመቻ ጥቅምት 9 እና 16/2009 ዓ.ም መካሄዱ ይታወቃል፡፡ይህ ዓይነቱ ገዳማዊ የሥራ ዘመቻ ለቤተ ክርስቲያን አዲስ ባይሆንም በተለይም በካቴድራሉ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መነኮሳቱ፤ካህናቱ፤ዲያቆናቱ ፤መዘምራኑ እና የአካባቢው ምእመናን በህብረት እንዲህ ዓይነቱ የህብረት ሥራ መሥራት ብዙም የተለመደ አልነበረም፡፡
በዓሁኑ ጊዜ በካቴድራሉ እየታየ ያለው የሥራ እንቅሥቃሴ የካቴድራሉ ልዩ ልዩ ሠራተኞች ህብረት/አንድነት ሊገነባ የሚችል በመሆኑ ለበረታታ ይገባዋል፡፡በተለይም በዚህ የሥራ ሂደት ሠራተኞቹ በራሳቸው ተነሳሽነት እና በጎ ፈቃድ እንዲህ ዓይነቱ በጎ ሥራ እንዲሠሩ ጉል ሚና የተጫወቱት የካቴድራሉ ዋና ፀሐፊ መ/ር ሰሎሞን በቀለ ሊመሰገኑ ይገባቸዋል፡፡
{flike}{plusone}