በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

የገብረ ሰላም በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ!!!

April 15, 2017

0035

በየዓመቱ በትንሣኤ ዋዜማ ሲከበር የቆየው የገብረ ሰላመ በዓል በዘንድሮው ዓመት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር ጎይቶኦም ያይኑ እና የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት ዛሬ ቅዳሜ ሚያዝያ 7 ቀን 2009 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡  በተረኛው ደብር በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ደብር ካህናት ጸሎተ ወንጌል ተደርሷል፡፡
“አሜሃ መልአ ፍስሐ ዓፉነ፤ ወተኀሥየ ልሳንነ፤ አሜሃ ይቤሉ አሕዛብ፡፡” በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን ሞላ፤ አንደበታችንም ሐሴትን ሞላ፤ በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ፡፡ መዝ. 125÷2 የሚለው የዳዊት መዝሙር በዲያቆዩ በዜማ ተዚሟል፡፡
ከዚያም በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 19 ላይ የተጻፈው የወንጌል ቃል በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በንባብ ተሰምቷል፤ በወንጌሉ እንደተጻፈው ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለበት ወቅት እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም እና ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በመስቀሉ ሥር ቆመው እንደበርና ኢየሱስ ክርስቶስም ከኀዘናቸው እንዳጽናናቸው ያብራራል፡፡
በመቀጠልም ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ ለዘተንሥአ እሙታን ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚል ያሬዳዊ መዝሙር በተረኛው በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ደብር ሊቃውንት ቀርቧል፤ ከዚያም አንሰ እረክብ ሰላመ በእንቲአሁ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ወልድ እሁየ ሊተ ወአነ ሎቱ አፈቅሮ እስከ አመ ፈቀደ የሚል ያሬዳዊ ወረብ በቅዱስ ዑራኤል ደብር ወጣቶች ቀርቧል፡፡ ከዚያም በማያያዝ ሁለት የቅኔ ሊቃውንት በዓሉን የተመለከተ ቅኔያት አቅርበዋል፡፡
በመቀጠልም በብፁዕ አቡነ እንድርያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ የበላይ ኃላፊ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል፡፡ ብፁዕነታቸው በሰጡት ትምህርት በኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ስደት እና ባርነት ተወግዷል፤ በነፍስ በሥጋ ተቆራኝተው የነበሩ አጋንንት ተበትነዋል፤ የ5500 ዓመት መከራ አልቋል፤ ምድርና ሰማያት ተቀድሰዋል፤ በፈጣሪ ደም ዓለም ተቀድሷል፤ ለሰው ልጆች ካሳ ተፈጽሟል፤ ልጅነት ተሰጥቷል፤ ይህች ዕለት በእግዚአብሔር ዘንድ የድኅነት እቅድ ተይዞባት የነበረች እለት ናት፤ ስብከተ ወንጌል በአራቱም ማዕዘን ተሰራጭቷል፤ መርገመ ሥጋ እና መርገመ ነፍስ ጠፍቷል፤ ይሁዳ ዘነፍስ በዓልህን አድርግ ተብሏል፤ የማናይ ታምራት አይቶ ስላመነ ከአባቱ ከአዳም ቀድሞ ገነት ገብቷል፤ በጨካኙ ጠላት ተይዘው የነበሩት ነፃነት ተሰብኮላቸዋል በማለት ብፁዕነታቸው ሰፋ ያለ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ ፖትርያርኩ ባስተላለፉት አባታዊ ትምህርት እና ቃለ ምዕዳን ዛሬ በዚህ ካቴድራል የተገኘነው የገብረ ሰላመን በዓል ለማክበር ነው፤ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙስና መቃብርን ያሸነፈበት በዓል ስለሆነ በዓሉ የሰላም በዓል ነው፤ የሰው ልጆች ከዘለዓለማዊ የሲዖል እሥራት የተፈቱበት በዓል ስለሆነ በዓሉ ትልቅ በዓል ነውና እንኳን ለዚህ ትልቅ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! በማለት አባታዊ ቡራኬ እና ቃለ ምዕዳን ካስተላለፉ በኋላ የሰላምና የነፃነት ምልክት የሆነውን ቄጤማ ከብፁዓን ሊቃ ጳጳሳት ጀምሮ በካቴድራሉ ለተገኙት ሊቃውንት እና ምእመናን በመስጠት የበዓሉን ምሥራች አብሥረዋል፡፡    
ምንጭ፡-www.addisababa.eotc.org.et

{flike}{plusone}

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/0035.jpg 2136 3216 tc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png tc2017-04-15 11:43:502017-04-15 11:43:50የገብረ ሰላም በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ!!!

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: የጸሎተ ሐሙስ ሕጽበተ እግር ሥርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናወነ Link to: የጸሎተ ሐሙስ ሕጽበተ እግር ሥርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናወነ የጸሎተ ሐሙስ ሕጽበተ እግር ሥርዓት በመንበረ ጸባዖት... Link to: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተለምዶ 22 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በመገንባት ላይ ያለውን የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሁለገብ ሕንጻ ጎበኙ!! Link to: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተለምዶ 22 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በመገንባት ላይ ያለውን የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሁለገብ ሕንጻ ጎበኙ!! ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተለምዶ 22 እየተባለ...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top