በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በአቢሲኒያ ባንክ በካቴደራሉ ቅጥር ግቢ የተሰራውን የእድሳት ገንዘብ ማሰባሰቢያ ማዕከል የካቴድራሉ አስተዳደር ፣ የአቢሲኒያ ባንክ ከፍተኛ የስራ ኋላፊዎችና የካቴደራሉ አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም የካቴድራሉ እድሳት ገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴ በተገኙበት የቁልፍ ርክክብ እና የምርቃት ሥነ-ሥርዓተ ተካሂዷል፡፡ የካቴድራሉ አስተዳደርም በአቢሲኒያ ባንክ በብዙ ወጪ ተገንብቶ የተሰራውን ማዕከል በመሰራቱ እና ለዚህ በመብቃቱ ለአቢሲኒያ ባንክ ከፍተኛ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ በማዕከሉም ለእድሳቱ ገቢ ለማድረግ እንዲሁም እድሳቱን በተመለከተ የሚሸጡ ሽያጮች የሚከናወኑበትና እድሳቱ ሲጠናቀቅም ቀጣይነት ያለው ሲሆን፤ ማዕከሉም በይፋ ለህዝበ ክርስቲያኑና ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጓል፡፡