በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን ለ5ኛ ጊዜ እረዳታ ተሰጠ

                                              በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

“ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፡፡” መዝ. 40÷1

“እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ”2ኛ ቆሮ. 9÷7

c

ከአሁን በፊት በዌብሳይታችን አማካኝነት ወጣት ብሩክ አስራት ከዛሬ 5 ወር በፊት ጀምሮ ለካቴድራሉ አረጋውያን የሚሆን በየወሩ ለአረጋውያኑ የሚያስፈልጋቸውን የምግብ እርዳታ እያደረገላቸው መሆኑን ስንዘግብ መቆየታችን የሚታወስ ሲሆን አሁንም እንደተለመደው 5ኛ ጊዜ ለ1 ወር አስቤዛ የሚሆን ከዚህ ቀጠሎ የተዘረዘሩትን ልኳል፡፡

100 ኪሎ ጤፍ

25 ሌትር ጋዝ፤

15 ሌትር ዘይት

15 ኪሎ ስኳር፤

15 ኪሎ በርበሬ፤

15 ኪሎ ሽሮ፤

5 ፓኬት ሻይ ቅጠል ፤5 ኪሎ ጨው እና 20 ሰሙና በእነ ወ/ሮ ማርታ ወርቄ፤በወንድሙ፤በወጣት ዳዊት መስፍን እና በጓደኞቹ አማካኝነት እርዳታውን የላከ ሲሆን ከ2 ወር በፊት በወ/ሮ ማርታ ወረቄ፤በወ/ሮ ሮማን እሸቴ፤በወ/ሮ የምስራች አበበና በወጣት ዳግማዊ መስፍን አማካኝነት የአረጋውያኑ መኖሪያ ቤት የሆነውን የንግስት ዘውዲቱ መታሰቢያ ቤት አንድ ቀን ማጽዳታቸው ይታወቀል፡፡

አሁንም ከአገር ቤት ተመልሶ ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ቀደም ሲል ቃል በገባው መሰረት 5ኛ ጊዜ ለአንድ ወር የሚሆን የወር አስቤዛ በወንደሙና በጓደኞቹ አማካኝነት እርዳታ ልኳል፡፡ በመጨረሻም በአባ ገ/ማሪያም ወ/ ሳሙኤል አማካኝነት ለወጣት ብሩክ አስራትና ለቤተ ሰዎቹ ጸሎትና ምስጋና ተደርጓል፡፡