አዲሱ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ (Bsc)
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ና በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ አማካኝነት ከሐምሌ 26 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. ጀምሮ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ኪሮስ ፀጋዬ ሲሆኑ እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባዔ፣ ካህናት፣ መዘምራን፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና የአጥቢየው ምእመናን በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጐላቸዋል፡፡
ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ኪሮስ ፀጋዬ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ቀደም ሲል በአገር ውስጥና ከሀገር ውጭ በተለያሉ ትላልቅ ገዳማትና አድባራት በዋና አስተዳዳሪነት ተመድበው ቤተ ክርስቲያኒቱን፤ማህበረ ካህናቱና ሕዝበ ክርስቲያኑን በአድነትና በስምምነተ ሲገለግሉ መቆየታቸው አብረዋቸው የመጡት የምስካዬ ሕዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም አስተዳዳሪ ከብዙ በጥቂቱ ተናግረዋል ፡፡
ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ኪሮስ ፀጋዬ ከዚህ በፊት በእልቅና/በዋና አስተዳዳሪት ያገለገሉባቸው ገዳማትና አድባራት፡-
1. በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ማርያም ቤ/ክ ፤
2. ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ፤
3. መንበረ መንግስት ቅ/ገብርኤል /
4. ሱዳን እና አውትራሊያ ውስጥ የሚገኙ የኢ/ኦ/ተ/አብያተ ክርስቲያናት ሲሆኑ
5. ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በዋና ዲን
6. በአሁኑ ሰዓት የእልቅና የመጨረሻ እድገት በሆነው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹሞዋል ፡፡
በክብረ በዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ የካቴድራሉ የበላይ ጠባቂና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንዲሁም የምስካዬ ሕዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም አስተዳዳሪና የመንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል ማህበረ ካናት የተገኙ ሲሆን በዓሉን አስመልክቶም ከመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራልና ከመንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል ሊቃውነት ቅኔ ቀርቧል፡፡
ዕለቱን አስመልክተው ጢሞቴዎስ አጠር ያለ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ብፁዕ አቡነ አረጋዊ የካቴድራሉ የበላይ ጠባቂና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በበኩላቸው ቤተክርስቲያን አንዲት ናት፣ ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ አባቶቻችን ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወሩ ቤተክርስቲያንና ህዝበ ክርስቲያንን ይመራሉ፣ ያስተምራሉ፣ ለዚህም ነው ዛሬ ሁለቱም አባቶቻችን (ወንድሞቻችን) ከመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ወደ ደብረ ገነት መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤልና ከመንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አንዲቷን ቤተክርስቲያን ለማገልገልና ሐዋርያዊ ተልዕኮአቸውን ለመፈፀም የተዛወሩት ብለዋል፡፡ምንም እንኳን የቦታው ስም ቢለያይም የቤተክርስቲያቱ አገልግሎት አንድ መሆኑን አበክረው ገልፀዋል፡፡
ከዚሁ ጋር አያይዘውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ከያዙት መንፈሳዊ እውቀት በተጨማሪ ዘመኑ የደረሰበትን እውቀት በመቅሰም ቤተ ክርስቲያኒቱና ሕዝበ ክርስቲያኑ በተሻለ መልኩ ሊያገለግሉ ይገባል ፤ቤተ ክርስቲያኒቱም የመልካም ሥራ ባለቤት በመሆኗ ሙስና እና ብልሱ አሠራርን በማስወገድ ረገድ የበኩሏን አስተዋፅኦ በመጣት ላይ እንደምትገኝ አክለው ገልፀዋል፡፡
{flike}{plusone}