በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በተለምዶ 22 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሕንፃ ግናባታው ተጀምሮ ቆሞ የነበረውን ሕንፃ ግንባታ ለማስጀመር የውል ሰነድ ተፈራረመ

November 4, 2015

                                                                                                                                              በመ/ር አምሃ ኃብቴ(BA)

01369

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባኤና ልማት ኮሚቴ ቀደም ሲል ከበጎ አድራጊው ክቡር በኵረ ምዕመናን ከበደ ተካልኝ 1634 ካሬ ሜትር ቦታ በስጦታ አግኝቶ በ1070 ካሬ ሜትሩ ላይ የሕንፃ ግንባታው ከተጀመረ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች ለተወሰኑ ዓመታት ቆሞ የቆየ ቢሆንም የዲዛይን ክለሳ ተደርጎለት በአሁኑ ሰዓት  ሕንፃውን ለማስጀመር ተገቢውን ሕጋዊ የጨረታ ሂደት ካከናወነ እና ከፈጸመ በኋላ ጥቅምት 20 ቀን 2008 ዓ.ም ጨረታውን ካሸነፈው ከባማኮን ኢንጂነሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር ጋር የውል ስምምነት ፈጸመ፡፡ የካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ከላይ ከተጠቀሰው ድርጅት ጋር የውል ስምምነቱን ሲፈጽም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተወካይ ልዑካን፣ የኤም ጂ ኤም ኮንሰልት ኃ.የተ.የግ.ማኅበር ተወካይ፣ የካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ፣ ልማት ኮሚቴ አባላትና የአስተዳደር ሠራተኞች በተገኙበት የፊርማ ስነ ሥርዓቱ ተከናውኗል፡፡
የሕንፃው አጠቃላይ ወጪ ብር ቫትን ጨምሮ 72‚280‚478.00 (ሰባ ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ ሰባ ስምንት ብር ብቻ) ሲሆን ነገር ግን የግንባታ ሥራው በሁለት ምዕራፍ እንዲሠራ ከተቋራጭ ድርጅቱ ጋር ስምምነት ላይ በመደረሱ ለመጀመሪያው ምዕራፍ ሥራ ውል ተፈጽሟል፡፡የመጀመሪያው ምዕራፍ ሥራው የሚያካትተው፡-
1.የኮንክሪት ሥራ ሙሉ ለሙሉ
2.የጣሪያ ሥራው ሙሉ በሙሉ
3.የግድግዳ ሥራ ማለትም ብሎኬትና ጡብ ሥራ በአጠቃላይ
4.የብረት ውቅር ሥራና ተያያዥ ሥራዎች በሙሉ
5.የልስንና ተያያዥ ሥራዎች በሙሉ
6.የመብራት መስመር ዝርጋታ 1-10.3 ድረስ
7.የንፁህ ውሃ አቅርቦትና የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ዝርጋታ ሥራዎች ከተራ ቁጥር 4-5 ድረስ ያካትታል፡፡ ይህንን ሥራ ለመሥራት አጠቃላይ ወጪው ከቫት በፊት ብር 27‚681‚604.80 (ሃያ ሰባት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ ስድስት መቶ አራት ብር ከሰማንያ ሳንቲም) ሲሆን ሥራውን ለማጠናቀቅ 365 ቀናት የሚያስፈልጉት መሆኑንም ስምምነት በተደረገበት ቀን ተገልጿል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የተቋራጭ ድርጅቱ ባለቤት ክቡር ኢንጂነር ግርማ ገላው  ከዚሁ ገንዘብ ላይ የ4% (የአራት በመቶ) ቅናሽ ያደረጉልን በመሆኑ ስለአደረጉልን ቅናሽ የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ክቡር ሊቀ ሥልጣናት አባ ገብረ ሥላሴ በላይ በካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ስም አመስግነው አጠር ያለ ትምህርት ከሰጡ በኋላ የፕሮግራሙ ፍጻሜ ሆኗል፡፡
የሕንፃው አጠቃላይ ይዘት ሕንፃው በ1070 ካሬ ሥፋት ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን ቤዝመንት፣ ምድር ቤት፣ መዳረሻ፣ አምስት ወለል (ፎቅ) እና  መዳረሻ (B+G+M+5+M)  ያለው ዘመናዊ ሕንፃ ነው፡፡
ሕንፃው የሚሰጠው አገልግሎት ሕንፃው ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ቤዝመንቱ ለመኪና ማቆሚያ (parking lot) ፣ ምድር ቤቱ ለባንከ፣ ለኢንሹራንስና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎት ለሚሰጡ ሥራዎች የሚሆን ሲሆን አምስቱ ወለሎች ደግሞ ለቢሮ፣ለሱቅ፣ አዳራሾችና ተያያዥ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎች ያሉት ነው፡፡

{flike}{plusone}

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/01369.jpg 480 640 tc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png tc2015-11-04 06:35:592015-11-04 06:35:59የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በተለምዶ 22 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሕንፃ ግናባታው ተጀምሮ ቆሞ የነበረውን ሕንፃ ግንባታ ለማስጀመር የውል ሰነድ ተፈራረመ

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: የእስክንድርያ ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ዳግማዊ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው Link to: የእስክንድርያ ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ዳግማዊ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው የእስክንድርያ ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ... Link to: እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ታቦተ ጽዮን Link to: እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ታቦተ ጽዮን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ታቦተ ጽ...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top