የጸሎተ ሐሙስ በዓል በመንበረ ጸበዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከበረ

የጸሎተ ሐሙስ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን የኢየሱስ ክርስቶስ ትህትና እየታሰበ በተለያዩ ስነ ስርኣቶች ተከብሮ ውሏል፡፡
ክርስቶስ በዛሬዋ እለት የሐዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በማጠብ ትህትናን እና ታዛዥነት ማስተማሩን በማሰብ ነው በዓሉ የሚከበረው።
በዛሬው ዕለትም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሥነ ስርዓቱ ሲከናወን ውሏል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን እግር፥ ጳጳሳቱ የቆሞሳቱን እና ካህናቱም የምዕመናኑን እግር በማጠብ የኢየሱስ ክረስቶስን አርአያነት ተከትለው ሥርዓቱን አከናውነዋል።