ስልክ፡ 011-1-23-35-18 / 011-1-23-35-15
Click here to add your own text
Click here to add your own text
ይህ ቲያትር ሙሉ ገቢው ለካቴድራሉ እድሳት ስለሆነ ሁሉም ሰው ሼር ያድርገው፡፡ በተጠቀሱት ቀናትም ይህንን በአይነቱ ለየት ያለውን ትውፊታዊ ቲያትር በመመልከት እውቀትዎን ያሳድጉ፡፡
Click here to add your own text
Click here to add your own text
ትምህርተ ሃይማኖት ዘቅድስት ሥላሴ
ለክርስትና ሃይማኖት መሠረቱ ማእከሉና መደምደሚያው ምሥጢረ ሥላሴ እንደሆነ ይታወቃል ምክንያቱም ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷም ነፍስን ነሥቶ ሰው ከሆነ በኋላ የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት የታወቀና የተረዳ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡ ይህም በዚህ በልደት እና በጥምቀት ሰሞን በቂ ትምህርት ሊሰጥበት የሚገባ ነው፡፡እግዚአብሔር ወልድ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ሆኖ በሥጋ ከመወለዱ በፊት […]
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሠራተኞች ልዩ የፅዳታ ዘመቻ አካሄዱ
የካቴድራሉ ልዩ ልዩ ሠራተኞች ጥቅምት 23/2009 ዓ.ም በካቴድራሉ ቅጥር ግቢ በዓይነቱ የተለየ የፅዳታ ዘመቻ በህብረት አካሂደዋል፡፡ይህ አባቢውን/ግቢውን የማጽዳት ሥራ ሲካሄድ ለ3ኛ ጊዜ ሲሆን 1ኛው እና 2ኛው የፅዳታ ዘመቻ ጥቅምት 9 እና 16/2009 ዓ.ም መካሄዱ ይታወቃል፡፡ይህ ዓይነቱ ገዳማዊ የሥራ ዘመቻ ለቤተ ክርስቲያን አዲስ ባይሆንም በተለይም በካቴድራሉ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መነኮሳቱ፤ካህናቱ፤ዲያቆናቱ ፤መዘምራኑ እና የአካባቢው ምእመናን በህብረት እንዲህ […]
የሐምሌ ሥላሴ በዓለ ንግሥ በመንበረ ጸባዖት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ!!
በየዓመቱ ሐምሌ 7 ቀን የሚከበረው የአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ መለኮታዊ በዓለ ንግሥ በዘንድሮው ዓመት 2008 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡ በበዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ እንድሪያስ የካቴድራሉ የበላይ ኃላፊ በቅዱስነታቸው መልካም ፈቃድ እለቱን አስመልክተው ሰፋ […]
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የ2008 ዓ.ም የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለበርካታ ችግረኞች ታላቅ የምሳ ግብዣ አደረገላቸው!!
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኘው የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እሑድ ሚያዚያ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ቁጥራቸው ከ1,000 በላይ ለሚሆኑ ነዳያን /ችግረኞች ሰፊ የሆነ የምሳ ግብዣ ያደረገላቸው መሆኑን የዝግጅት ክፍላችን ከቦታው ድረስ በመሄድ አረጋግጧል፡፡ ይህ ታላቅ የምሳ ግብዣ የተከናወነበት ቦታ ቀደም ሲል በነገሥታቱ፣ በመሳፍንቱ፣ በመኳንንቱና በደጅአዝማቾቹ ዘመን በተመሠረተውና 107 ዓመት እድሜ ባስቆጠረው የካቴድራሉ የሰንበቴ […]
የግብረ ሰላም በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጰሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች፤የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅና የክፍል ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት ቅዳሜ ሚያዝያ 22 ቀን 2008 ዓ.ም የግብረ ሰላም በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ ለዘተንስአ […]