በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

ዓመታዊው የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ

January 16, 2021

ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ጢሞቲዎስ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሰይፈ፣ የአራዳና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ መ/አሚን አባ ላዕከ ማርያም፣ የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሲራክ እንዲሁም የደብሩ ማኅበረ ካህናትና እጅግ በርካታ ኦርቶዶክሳዊ ምእመናን በተገኙበት የእግዚአብሔርን ክብር በሚገዳደር መልኩ በሰናዖር ሜዳ ላይ የተሠራውን ሕንጻ ሰናዖር እግዚአብሔር ያፈረሰበትንና መግባቢያ ቋንቋቸውንም የደባለቀበትን ዕለት በሚዘከርበት ሁኔታ በድምቀት ተከብሯል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የዕለቱን ታሪክ የተመለከተ ሰፊ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን በእኛም ዘመን የእግዚአብሔርን ክብር የሚጋፋ የትኛውም ዓይነት ክፉ ተግባር እንዳናከናውን ደግሞም በሕይወታችን ያለውን የኃጢአት ክምር በንስሐ እናፈርሰ ዘንድ መልእክት ተላልፏል፡፡

በመቀጠልም ካቴድራሉ በ1924 ዓ.ም ተመስርቶ በ1936 ዓ.ም መንፈሳዊ አገልግሎት መጀመሩና ለረጅም ጊዜያት ማለትም ለሰባ ሰባት ዓመታት ያክል አገልግሎት በመስጠቱ የተነሣ በከፍተኛ ጉዳት ውስጥ እንደሚገኝ ተገልፆ በአሁኑ ስዓት ግን ይህንን ታሪካዊና መንፈሳዊ ቅርስ ለመታደግና የዕድሳት ሥራ ለመሥራት ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገርና ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች እንደ ተዋቀረና በእንቅስቃሴ ላይም እንደሚገኝ በቀረበው ሪፖርት ላይ ተደምጧል፡፡

በመጨረሻም የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የዕለቱ ትምህርት በሰፊው ተሰጥቷልና ይበቃናል፣ የሰማነውን በሕይወት እናኑረው፣
ይህ ትልቅ ካቴድራል ከመንፈሳዊ ቦታነቱም ባሻገር የቤተ ክርስቲያናችንን ብሎም የሀገራችንን ታሪክ ጠገብነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፣ ስለሆነም የተጀመረው የዕድሳት እንቅስቃሴ የሕንጻውን ታሪካዊ ማንነት በጠበቀ መልኩ መታደስ ይኖርበታል፣ ለዚህም መልካም ተግባር ሀገረ ስብከታችን በአስፈላጊው ነገር ሁሉ ከእናንተ ጋር ነው በማለት አረጋግጠዋል።
የጥምቀት በዓልም ኦርቶዶክሳዊ ጨዋነት በተላበሰ መልኩ እንዲከበር ለሕዝበ ክርስቲያኑ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ ፦አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ድረ-ገጽ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/FB_IMG_1610756936845.jpg 720 960 htc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png htc2021-01-16 06:26:492021-01-16 06:26:52ዓመታዊው የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: ወርሐዊ የአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ክብረ በዓል ባማረ ሁኔታ ተከበረ Link to: ወርሐዊ የአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ክብረ በዓል ባማረ ሁኔታ ተከበረ ወርሐዊ የአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ክብረ በዓል ባማረ... Link to: of Holy Trinity Church in Addis Ababa, Ethiopia Link to: of Holy Trinity Church in Addis Ababa, Ethiopia of Holy Trinity Church in Addis Ababa, Ethiopia
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top