የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት እና የጥገና ስራ አጠቃላይ ሪፖርት እስከ ነሐሴ 2015ዓ/ም

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ የእድሳት እና የጥገና ስራ አጠቃላይ ሪፖርት እስከ ነሴ 2015 ዓ/ም

1ኛ መሰረታዊ የኮንትራት ስምምነቱ መረ

  1. የስራው ባለቤት          መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥነላሴ ካቴድራል አስተዳደር
  2. የስራው ተቋራጭ ቫርኔሮ ኮንስትራክሽን  .
  3. አማካሪ መሃንዲስ ፋሲል ጊዮርጊስ ኢንጅነርስ እና አርክቴክት
  4. የአማካሪው ተጠሪ ፋሲል ጊዮርጊስ
  5. ኮንትራቱ የተፈረመበት ቀን መስከረም 11/2015
  6. የሳቭት ርክክብ የተካሄደበት ቀን መስከረም 25/2015
  7. ስራ የመጀመሪያ ቀን መስከረም 30/2015
  8. የኮንትራት ዓይነት የጥቅል ዋጋ
  9. አጠቃላይ የኮንትራት ጊዜ 545 ቀናት
  10. የመሰረታዊ ስራዎች የኮንትራት ዋጋ/ ቫትን ጨምር / ብር          164,715,207.23
  11. እንዳስፈላጊነቱ ለሚሰሩ ሥራዋች የኮንትራት ዋጋ /ቫትን ጨምሮ/ ብር  7,784,792.77
  12. አጠቃላይ ሁሉንም ያካተተ የኮንትራት ዋጋ / ቫትን ጨምር/ ብር 172,500,000.00
  13. በኮንትራክተሩ በአንዱ ጊዜ ለክፍያ የሚቀርበው ትንሹ ክፍያ የኮንትራቱ 10 %
  14. ከኮንትራክተሩ ከየክፍያው ላይ የሚቀነስ የጥገና ዋስትና ገንዘብ የኮንትራቱ 5 %
  15. ለኮንክትራክተሩ ለስራ ማስኬጃ የተፈቀደ ቅድመ ክፍያ                         የኮንትራቱ 10 %
  16. ለተፈቀደው ቅድመ ክፍያ ከየክፍያው ላይ የሚቀነስ           የክፍያው 12.5 %
  17. የሰራዋስትና ከኢንሹራንስ የተሰጠ / ብር /      17,200,000.00/የኮንትራቱ 10 % /
  18. እስከ አሁን ስራው የወሰደው ጊዜ          264 ቀናት
  19. እስከ አሁን ስራው የወሰደው ጊዜ በፐርሰንት          44 %
  20. ኮንትራክተሩ ቅጣት ውስጥ ቢገባ በየቀኑ የሚቀጣው           የኮንትራቱ 0.01 %
  21. ኮንትራክተሩ ቅጣት ውስጥ ቢገባ የሚቀጣው የቅጣት ጣራ            የኮንትራቱ 10 %
  22. ኮንትራቱ የሚያበቃበት ጊዜ             30/7/2016
  23. ተጨማሪ የተሰጠ ጊዜ             የለም
  • ስራው ከተጠናቀቀ በኃላ የሙከራ ጊዜ  365 ቀን / 1 ዓመት/

 

2 ሪፖርቱ እስከ ቀረበበት ጊዜ ድረስ የተሰሩ ስራዎች

ሀ/ የዋናው ጉልላት ፣ የመስቀል ፣ የመዋቅር (  የስትራክቸር  )  ጥገና እና እድሳት የልስን ስራ እና የድንጋይ ማጽዳት እና ዋነኞቹ የተከናወኑ ስራዋች ሲሆኑ እነዚህ ስራዎች በዝርዝር ከዚህ በታች ተቀምጠዋል ፡፡

የዋናው ጉልላት ጥገና የጉልላቱን የውስጥ አካል ማጽዳት ፣ የተነደሉ የጉልላቱ ሽፋን መደቦችን መቀየር እና መጠገን ፣ የጉልላቱን የእንጨት እና የብረት የተሸካሚ ማዋቅር መቀየር እና ማጠናከር ብረቶችን የዝገት መከላከያ እንጨቶቹን የእንጨት ቀለም መቀባት የውሃ ስርገት እና የሙቀት መከላከያ ማዱረግ እና የሶስት መስቀሎች ጥገና የካንክሪት እና የብረት ኮለን   የሶሌታ  አና የቢም  ማጠናከር ሥራዋች የልስን ስራ የቁርቀር ስራ የዱንጋይ እጥበት ዋነኖቹ የስራ አይነቶች ናቸው ፡፡

ከላይ ከተዘረዘሩት ስራዎች

  1. የጉልላት ጥገና 85 % ፣
  2. የስትራክቸር / የመዋቅር / ማጠናከር ስራ 90 % የተጠናቀቀ ሲሆን ፤ የቤተክርስቲያኑ የውስጥ የፎቅ ወለል / ሜዛኒን / 100 % ተጠናቋል ፣
  3. የመስቀሎቹ የጥገና ስራ 97 %፣
  4. የውጪ የልስን ስራ ሁለት እጅ 95 % የተጠናቀቀ ሲሆን ፣
  5. የአርች የማጠናከር ስራ 100 % ተጠናቋል ፣
  6. የብረት የውስጥ ደረጃዎች ጽዳት እና ጥገና ፣
  7. የድንጋይ እጥበት የመጀመሪያ ደረጃ እና ፣
  8. የምዱር ቤት የኤሌክትሪክ እና የፍሳሽ ዝርጋታ ስራ ከሌሉቹ ከላይ ከተዘረዘሩት ስራዎች በተጓዳኝነት በመካሄዱ ላይ ይገኛሉ ፡፡

3ኛ በቅርቡ የሚመሩ እስከ አሁን ያልተመሩ  ( በጥቂቱ የተሰሩ  ) ስራ

  • የስእል ጥገና ፣
  • የመዳብ ቀለም ቅብ ፣
  • የዱንጋይ ጥገና ፣
  • የካቴዱራሉ ዙሪያ የዱንጋይ ንጣፍ ስራ ፣
  • በምስራቅ አቅጣጫ ያሉ የወለል የማጠናከር ስራ ፣
  • የሁለቱ ደወሎች የመዋቀር የማጠንከር ስራ ፣
  • የፍሳሽ መስመር ሥራ ፣
  • ከጉልላቱ ስር ያሉ ጣራዎች ላይ የሚሰራ የውሃ ስርገት መከላከያ
  • የዓውደምህረት ጥገና ፣
  • የመስታወቅ ስእሎት ጥገና ፣
  • የመጨረሻ / ሶስተኛ / ክፍል የልስን ስራ ፣
  • የግድግዳ እና የጣራ ቀለም ቅብ ፣

4ኛ ማጠቃለያ

የካቴድራሉ የእድሳት እና የጥገና ስራ ከተጀመረ 326( 59.82%) ቀናትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ አካላዊ ( ፊዚካል) የስራው አፈጻጸም ከ 36% በላይ ፣ በገንዘብ ( ፋይናንሺያል)  አፈጻጸሙ ደግሞ 20% ደርሷል ፡፡

ኮንትራክተሩ ስራውን ከጀመረ እስከ ዛሬ ዱረስ ሁለት ክፍያዎችን የወሰደ ሲሆን ፣ በሁለቱ ክፍያዎች አጠቃላይ የተከፈለው የገንዘብ መጠን ቫት (15%) ፣ የዋስትና መያዠ (5%) እና የወቅቱ የኦላር ምንዛሬ የታሰበበት ብር 27፣436,583.42 /ሃያ ሰባት ሚሊየን አራት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ ሶስት ብር ከ 42/100 / ነው ፡፡

በአገር ደረጃ የተከሰተው የሲሚንቶ እጥረት በኘሮጀክቱ ላይ የገጠመ ዋነኛ ችግር ቢሆንም እንኳን ኮንትራክተሩ እየወሰደ ባለው የራሱ ቀና አካሄዶች የኘሮጀክቱ ስራ እስካሁን በእጥረቱ ምከንያት አልተስተጓጉለም ፡፡

እስከ አሁን ሪዓርቱ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ከኮንትራክተር ምንም አይነት የገንዘብ እና የጊዜ ተጨማሪ የማካካሻ ቅሬታ / ከሌም / አልቀረበም በመሆኑም የጥገናው ስራ በተያዘለት ጊዜና በጀት ይጠናቀቃል ተብሎ ይታመናል ፡፡

 

አዘጋጅ / አማካሪ መሃንዲስ / ፋሲል ጊዮርጊስ መሃንዲሶች እና አርክቴክቶች