በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ልዩ እድሳት እንደሚያስፈልገው ተገለፀ፡፡

November 25, 2012

                   በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጽ/ቤት እንደገለፀው የካቴድራሉ ህንፃ ወስጣዊም ሆነ ውጫዊው ክፍሉ ከጊዜ ብዛት የተነሳ የመሰነጣጠቅ ሁኔታ እየታየበት በመምጣቱ አስቸኳይ የሆነ ሙሉ እድሳት እንደሚያስፈልገውና ጥናቱ በጥንቃቄ እንዲጠና ከበላይ አካልም ጭምር ስለታነበት በባለሞያዎች በምን ዓይነት ሁኔታ መታደስ እንዳለበት ከመጋቢት 2ዐዐ4 ዓ.ም ጀምሮ ጥንቃቄ በተሞላበት ሙሉ ጥናት ሲደረግበት ቆይቶ ሕዳር 15/03/2005 ዓ.ም ዶ/ር ብፁእ አቡነ ገሪማና ብፁእ አቡነ አረጋዊ በተገኙበት ለካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር፤ለካቴድራሉ ልማት ኮሚቴና ለተለያዩ ምሁራን በነኢንጂነር ቀሲስ ደመቀ አማካኝነት ሙሉ ጥናቱ ቀርቧል፡፡ካቴድራሉን ለማደስ የባለሙያዎች አስተዋጽኦ ወሳኝ በመሆኑ በአስተዳደሩ አማካይነት የተለየዩ አዳዲስ ባለሙያዎች በልማት ኮማቴው እንዲሳተፉ ተደርጎ ካቴድራሉ በምን መልኩ መታደስ እንዳለበት ሰፊ ጥናት ሲያደርጉ ቆይቷል በማድረግ ላይም ናቸው፡፡ ውጤቱ ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ለካቴድራሉ ሰበካ ጉባዔና ልማት ኮሚቴ እንዲሁም ለተለያዩ ምሁራን የቀረበ ሲሆን ቀደም ሲል ጥናቱ ለቅዱስ አባታችን በሕይወት እያሉ ቀርቦ ጥሩ አድናቆት ተችሮት እንደነበር ከአንዳንድ የካቴድራሉ ሠራተኞች ለማወቅ ተችሏል፡፡ በገቢ ማሰባሰቢያ ረገድም በካቴድራሉ አውደ ምህረት ሲነገረ የቆየ ሲሆን በተለይም መጋቢት 1ዐ ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም እና ሰኔ 24 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም በካቴድራሉ ሁለገብ አዳራሽ የስብከተ ወንጌልና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ተካሂዶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ከዚህም በተጨማሪ በካቴድራሉ ዌብ ሳይትና በካቴድራሉ ዐውደ ምህረት ላይ በሰፊው ሲገለጽ መቆየቱም አይዘነጋም፡፡

   

ልማትን በተመለከተ

 

በአሁኑ ወቀት የካቴድራሉን ሁለንተናዊ ችግር ሙሉ በሙሉ ይፈታል ተብሎ የተገመተው በ22 ማዞሪያ አካባቢ በ47,ዐዐዐ,ዐዐዐ.ዐዐ (አርባ ሰባት ሚሊዮን ብር) አዲስ ባለ አራት ፎቅ ዘመናዊ ሁለገብ ሕንፃ እያስገነባ ሲሆን ነገር ግን ሥራው ቀደም ሲል ከ3 ዓመታት በፊት መሬቱ እንዳይወሰድ ሲባል ብቻ የተጀመረ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን ያን ያህል ገንዘብ አግኝቶ ሥራውን ለመሥራት ካቴድራሉ እጅግ በመቸገሩና ከአቅሙ በላይ በመሆኑ ከባለቤቶቹ ምእመናን ጋር በመወየየትና የተለያዩ አማራጮችን በማመቻቸት ላይ ይገኛል፡፡በመሆኑም ጉዳዩ የሁሉም ምእመን ጉዳይ በመሆኑ ምእመናንበገንዘባቸውና በእውቀታቸው የቻሉትን የህል የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ቤተክርስቲያኒቱ ጥሪዋን በማስተላለፍ ላይ ትገኛለች፡፡

           

 

የካቴድራሉ መቃብር ሥፍራ ከዓመታት በፊት በማለቁ ምክንያት ምእመናን በመቸገር ላይ መሆናቸው ለሁላችን ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም ጊዜያዊ መፍትሔ ይሰጥ ይሆናል ተብሎ በካቴድራሉ ቅፅረ ግቢ በብር 7ዐዐ,ዐዐዐ.ዐዐ (ሰባት መቶ ሺህ ብር) ወጭ ዘመናዊ የቀብር ፉካ እያሰራ እያሠራ ቢሆንም ዘላቂ መፍትሔ ለማግኘት ግን በመቃብር ዙሪያ የሚያጠና ኮሚቴ ተዋቅሮ ሥራውን በመሥራት ላይ ሲሆን ከአርበኞች ጋርም የቤተ ክርስቲያኒቱና የህዝበ ክርስቲያኑ ችግር ሊፈታ በሚችል መልኩ በሰፈው እየተመካከሩበት ይገኛል ፡፡በመሆኑም ምእመናን ሐሳባቸውና አስተያየታቸውን እንዲሁም ምን መሠራት እንዳለበት በአካልና በካቴድራሉ ዌብ ሳይት ባለው አድራሻ በመጠቀም የበኩላቸውንአስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

 

  በአጠቃላይ ካቴድራሉን በየትኛውም ዘርፍ መርዳት ለሚፈልጉ ምእመናን በአካልና በካቴድራሉ ውብሳይት ባለው    አድራሻና የባንክ አካውንት በመጠቀም ካቴድራሉን ለማደስ መርዳት የምችሉ መሆኑንና እንዲሁም በካቴድራሉ ጽ/ቤት በአካል እየመጡ ችግሩን እያዩ የሚስፈልገውን ማቴሪያልም ይሁን ገንዘብ የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል፡፡

 

   

 

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/img_0044.jpg 480 640 tc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png tc2012-11-25 18:03:472012-11-25 18:03:47የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ልዩ እድሳት እንደሚያስፈልገው ተገለፀ፡፡

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን ለ2ኛ ጊዜ የምግብ እህል እረዳታ ተሰጠ Link to: በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን ለ2ኛ ጊዜ የምግብ እህል እረዳታ ተሰጠ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ... Link to: በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን ለ3ኛ ጊዜ እረዳታ ተሰጠ Link to: በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን ለ3ኛ ጊዜ እረዳታ ተሰጠ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top