በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን ለ2ኛ ጊዜ የምግብ እህል እረዳታ ተሰጠ

November 25, 2012

   

የዛሬ ሁለት ሣምንት አካባቢ ወጣት ብሩክ አስራት ከአሜሪካን አገር መጥቶ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በንግስት ዘውዲቱ መታሰቢያ ቤት ተጠልለው ለሚኖሩ 15 አረጋወያን በአካል ተገኝቶ የአረጋውያኑ የአኗኗር ሁኔታ እንደጎበኘና ለጊዜው የሚስፈልጋቸውን ልዩ ልዩ የአንድ ወር የምግብ አስቤዛ እርዳታ እንዳደረገላቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡

 

 

አሁንም ከአገር ቤት ተመልሶ ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ቀደም ሲል ቃል በገባው መሰረት ለሁለተኛ ጊዜ ለአንድ ወር የሚሆን የወር አስቤዛ በወንደሙና በጓደኞቹ አማካኝነት

                   100 ኪሎ ጤፍ፤

                   1 ኩንታል ከሰል፤

                   15 ሌትር ዘይት፤

                   15 ኪሎ ስኳር፤

                   15 ኪሎ በርበሬ፤

                   15 ኪሎ ሽሮ፤

                  5 ኪሎ ጨው፤

                  5 ፓኬት ሻይ ቅጠል፤

                  15 ሰሙና ለአረጋውያኑ እርዳታው እንዲደርሳቸው አድርጓል ፡፡

 

በዚሁ ዕለት በክቡር ሊቀ ሥልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ አማካኝነት ለወጣት ብሩክ አስራት ቤተሰዎችና ለጓደኞቹ ጸሎትና ምስጋና እንዲሁም ቃለ ምእዳን ተሰጥተዋል ክቡር ሊቀ ሥልጣናት ኣባ ገ/ሥላሴ በላይ እንደገለፁት እንደ እነዚህ የመሰለ አቅመ ደካማ የሆኑ አረጋውያን መርዳትበእግዚአብሔር ዘንድ ወጋው እጅግ በጣም ትልቅ መሆኑን ገልፀው በተለይም በካቴድራሉ ቅፅረ ግቢ በንግስት ዘውዲቱ መታሰቢያ ቤት ተጠልለው የሚኖሩ አረጋውያን 24 ሰዓት እግዚአብሔር ሲለምኑ የመኖሩና እግዚአብሔር በሰዎች ላይ አድሮ የዕለት ጉርስ ከሚሰጥዋቸው ምዕመናን ውጭ ምንም ዓይነት ረዳት እንደሌላቸውና በአንዲት ጠባብ ቤት እስከ 8 የሚሆኑ አረጋውያን እናቶች ተጨናንቀው እንደሚኖሩና የምግብ ችግር ብቻ ሳይሆን የመፀዳጃ፤የማዕድ ቤት፤ የውሀና የንጽህና ችግርም እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም እነዚህ አረጋውያን እደሚያቸው ከ75 እስከ 98 ከዚያ በላይ በመሆኑ ራሳቸውን ችለው ምግብ ለማብሰልም ሆነ ለመንቀሳቀስ እንደሚያቅታቸውና ከሚኖሩበት ቤት ለመውጣትም ሆነ ለመግባት እንደሚቸገሩ ገልፀው አረጋውያኑን ልትመግብ፤ ልትንከባከብና ንጽህናቸውን ልትጠብቅ የምትቸል ሰራተኛ እንደሚያሰፈልጋቸው ክቡር ሊቀ ሥልጣናት ገልፀዋል ፡፡በመጨረሻም በወጣት ብሩክ አስራት ለተደረገው ነገር ሁሉ ምስጋናቸው እጅግ የላቀ መሆኑን ገልፀው ሌሎችም የዚሁ የተቀደሰ ዓላማ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

 

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/img_0001.jpg 480 640 tc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png tc2012-11-25 15:15:212012-11-25 15:15:21በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን ለ2ኛ ጊዜ የምግብ እህል እረዳታ ተሰጠ

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን እረዳታ ተሰጠ Link to: በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን እረዳታ ተሰጠ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ... Link to: የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ልዩ እድሳት እንደሚያስፈልገው ተገለፀ፡፡ Link to: የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ልዩ እድሳት እንደሚያስፈልገው ተገለፀ፡፡ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ልዩ እድሳት...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top