ሰበር ዜና
ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢትየጽያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ስድስተኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመረጡ፡፡ ከ806 ድምጽ 500 ውን በማግኘት ፓትርያርክ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ መሠረት ብፁዕ አቡነ ማትያስ 500 ድምፅ በማግኘት 1ኛ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ 98 ድምፅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 98 ድምፅ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በ70 ድምፅ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ 39 ድምፅ በዚህም መሠረት ብፁዕ አቡነ ማትያስ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በመንበረ ተክለ ሃይማኖት የሚሾሙ ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ይኾናሉ፡፡ በዐለ ሲመቱም እሁድ የካቲት 24/2005 ዓ.ም በመንበረ ጸበዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የፈፀማል፡፡