የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ዘመናዊ ሁለ ገብ የመቃብር ፎካ ለመስራት የውል ስምምነት ተፈረመ

0050

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባኤና ልማት ኮሚቴ ሊያሠራው ላቀደው ሁለ ገብ የመቃብር ፎካ ህንፃ መስከረም 12/2006 ዓ.ም በሪፖርተር ጋዜጣ ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ከ11 ያላነሱ ተጫራቾች/ተወዳዳሪዎች የቀረቡ ሲሆን የካቴድራሉ የቴክኒክ ኮሚቴው ያወጣውን መስፈርት አሟልተው ለውድድር የቀረቡት/ያለፉት ግን 3 ድርጅቶች ነበሩ፡፡እነሱም
1.    አንኮር ኮንስትራክሽን ደረጃ 4 ሲሆን ያቀረበው የገንዘብ መጠን 7,035,597.76
2.    አምባቸው አስገዶም  ኮንስትራክሽን ደረጃ 5 ሲሆን ያቀረበው የገንዘብ መጠን 7,162,287.20 እና
3.    ኤ.ቢ.ኤም. ኮንስትራክሽን ደረጃ 3 ሲሆን ያቀረበው የገንዘብ መጠን 7,024,235.18 ነው፡፡
በመሆኑም ሥረውን ከመጀመሪያው ጀምሮ ሲከታተሉ የቆዩት የሀገረ ስብከት ተወካዮች፤የካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤና ልማት ኮሚቴ በጋራ በመሆን ተወዳዳሪዎቹ ያቀረቧቸውን ዶክሜንቶች፤ደረጃና የገንዘብ መጠን በካቴድራሉ  ባለሞያዎች  ቴክኒክ ኮሜቴ ተሠርቶ ከቀረበ በኋላ ኤ.ቢ.ኤም. አንኮር ኮንስትራክሽን ከቀረቡት ተወዳዳሪዎች መካከል ከሁሉም የተሻለ ደረጃ ያለውና ያቀረበው የገንዘብ መጠንም ከሁሉም ያነሰ በመሆኑ  ኤ.ቢ.ኤም ኮንስትራክሽንን አሸናፊ አድርጎ መርጦታል፡፡በመሆኑም ህዳር 20/2006 ዓ.ም ይህን አስመልክቶ የውል ስምምነቱ ላይ  የሀገረ ስብከት ተወካዮች፤የካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤና ልማት ኮሚቴ እንዲሁም የኤ.ቢ.ኤም. ኮንስትራክሽን ተወካይ በተገኙበት የውል ስምምነቱ ተፈርሟል፡፡

ሥራው በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚያልቅ ሲሆን ከፎካው ጋር ተያያዥ ያላቸው ሥራዎች ከላይ በተጠቀሰው የገንዘብ መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ይደረጋል፡፡ ኤ.ቢ.ኤም.  ኮንስትራክሽን ከ7,024,235.18  ብር ላይ 24,235.18 ብር በመቀነስ በ7,000,000 ብር ብቻ እንደሚሠራ ተስምምቷል የውሉ አካል እንዲሆንም ተደርጓል፡፡

የዕለቱ መርሃ ግብርም በክቡር ቆሞስ ሊቀ ሥልጣናት አባ ኪሮስ ፀጋዬ የካቴድራሉ ዋና አስዳዳሪ በፀሎት ተዘግቷል፡፡

{flike}{plusone}