በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳደር ጽ/ቤት በካቴድራሉ ግቢ ውጥ በአ/አ ሀ/ስብከት መዋቅራዊ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር ጥናት ላይ በመቃውሞ ድብቅ ስብሰባ ተካሂዷል ተብሉ የተዘገበውን በፅኑ ተቃወመ

December 17, 2013

pp002

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል  አስደናቂ ከሚባሉ ታሪካዊ ቦታዎች አንዱ ነው፡፡ ካቴድራሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ዓለም ዓቀፋዊ ይዘት ያለውና አንጋፋ ካቴድራል ሲሆን ከታሪካዊነቱም በተጨማሪ፡-
•    ዓለም አቀፋዊ የኃይማኖት ስብሰባዎች የሚካሄድበት፣
•    የፓትርያሪኮችና የብፁአን ለቃነ ጳጳሳት በዓለ ሲመት የሚከናወንበት፣
•    ብሔራዊ የመታሰቢያ በዓላትና ሥርዓተ ፀሎት የሚካሄድበት ነው፡፡
ከ6ቱ ቅዱሳን ፓትርያሪኮች መካከል 4ቱ የካቴድረሉ አገልጋዮችና የሥራ ኃላፊዎች የነበሩ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት የካትድራሉ አስተዳዳሪዎችና አገልጋዮች የነበሩ ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ይህም ካቴድራሉ ምን ያህል ትልቅ ቦታ እንደሆነና በቦታውም የሚመደቡ ሰዎች ምን ያህል ሊቃወንት እና የልማት አባቶች እንደሆኑ ግልፅ ነው ፡፡

ይሁንና ግን  የታላቁና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሂዶ ቤተ ክርስቲያን መኩሪያና መመከያ የሆነውን  ካቴድራል ስም ለማጥፋት December 14, 2013 ሐራ ዘተዋሕዶ በሚባል ብሎግ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳደር ጽ/ቤት በካቴድራሉ ግቢ ውጥ በአ/አ ሀ/ስብከት የመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር ጥናት ላይ በመቃውሞ ድብቅ ስብሰባ ተካሂዷል ተብሎ መዘገቡ እጀግ በጣም የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ከእውነት የራቀ ውሸት መሆኑን የካትድራሉ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡የብሎጉ አዘጋጆቹም ከእንዲህ አይነት ከእውነት የራቀ የአልቧልታ ሥራ እንዲታቀቡ በእግዚብሔር ስም ጠይቋል፡፡ካቴድራሉ አዲሱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መዋቅራዊ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር ጥናት ከየትኛውም ደብር /ካቴድራል ቀድሞ ሀገረ ስብከቱ ለሚያስተዳድራቸው ገደማትና አድባራት በተለይም የመልካም አስተዳደር ችግር ላለባቸው አንዳንድ  ገደማትና አድባራት ትክክለኛና ወቅታዊ መሆኑን ቀድሞ የተረዳ መሆኑን ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብሏል፡፡   
አጠቃላይ የካቴድራሉ የአሠራር ሂደት አሁን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከተዘጋጀው መዋቅራዊ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር ጥናት ቀደም ብሎ ከዓመታት በፊት በሥራ የተረጎመና አስከአሁንም ድረስ በዚሁ የአሠራር ሂደት እንደቀጠለ ነው፡፡ለዚሁም ነው ካቴድራሉ ልማታዊ ካቴድራል ሊሆን የቻለው፡፡በአሁኑ ሰዓት ካትድራሉ በተለምዶ 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ47ሚሊዮን ዘመናዊ በለ5 ፎቅ ሁለ ገብ ህንፃ እያስገነባ ሲሆን እንደዚሁም በካቴድራሉ አከባቢ በ7,000,000 ሁለ ገብ የመቃብር ፎካ በመገንባት ላይ ነው፡፡

በመሆኑም ታሪካዊና ልማታዊ የሆነውን የካቴድራሉን ስሙን ለማጥፈት ብሎም የጀመረውን የልማት እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ መሆኑን ሁሉም የቤተ ክርስቲኒቱ አባቶች፤ሊቃውንት፤አገልጋዮችና ምዕመናን እንዲገነዘቡልን እንፈልጋለን በማለት አሳስቧል፡፡

{flike}{plusone}

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/pp002.jpg 469 640 tc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png tc2013-12-17 14:49:452013-12-17 14:49:45የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳደር ጽ/ቤት በካቴድራሉ ግቢ ውጥ በአ/አ ሀ/ስብከት መዋቅራዊ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር ጥናት ላይ በመቃውሞ ድብቅ ስብሰባ ተካሂዷል ተብሉ የተዘገበውን በፅኑ ተቃወመ

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ዘመናዊ ሁለ ገብ የመቃብር ፎካ ለመስራት የውል ስምምነት ተፈረመ Link to: የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ዘመናዊ ሁለ ገብ የመቃብር ፎካ ለመስራት የውል ስምምነት ተፈረመ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ... Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2006 ዓ.ም የልደት በዓልን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2006 ዓ.ም የልደት በዓልን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top