በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ዘመናዊ ሁለ ገብ የመቃብር ፎካ ለመስራት የውል ስምምነት ተፈረመ

December 1, 2013

0050

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባኤና ልማት ኮሚቴ ሊያሠራው ላቀደው ሁለ ገብ የመቃብር ፎካ ህንፃ መስከረም 12/2006 ዓ.ም በሪፖርተር ጋዜጣ ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ከ11 ያላነሱ ተጫራቾች/ተወዳዳሪዎች የቀረቡ ሲሆን የካቴድራሉ የቴክኒክ ኮሚቴው ያወጣውን መስፈርት አሟልተው ለውድድር የቀረቡት/ያለፉት ግን 3 ድርጅቶች ነበሩ፡፡እነሱም
1.    አንኮር ኮንስትራክሽን ደረጃ 4 ሲሆን ያቀረበው የገንዘብ መጠን 7,035,597.76
2.    አምባቸው አስገዶም  ኮንስትራክሽን ደረጃ 5 ሲሆን ያቀረበው የገንዘብ መጠን 7,162,287.20 እና
3.    ኤ.ቢ.ኤም. ኮንስትራክሽን ደረጃ 3 ሲሆን ያቀረበው የገንዘብ መጠን 7,024,235.18 ነው፡፡
በመሆኑም ሥረውን ከመጀመሪያው ጀምሮ ሲከታተሉ የቆዩት የሀገረ ስብከት ተወካዮች፤የካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤና ልማት ኮሚቴ በጋራ በመሆን ተወዳዳሪዎቹ ያቀረቧቸውን ዶክሜንቶች፤ደረጃና የገንዘብ መጠን በካቴድራሉ  ባለሞያዎች  ቴክኒክ ኮሜቴ ተሠርቶ ከቀረበ በኋላ ኤ.ቢ.ኤም. አንኮር ኮንስትራክሽን ከቀረቡት ተወዳዳሪዎች መካከል ከሁሉም የተሻለ ደረጃ ያለውና ያቀረበው የገንዘብ መጠንም ከሁሉም ያነሰ በመሆኑ  ኤ.ቢ.ኤም ኮንስትራክሽንን አሸናፊ አድርጎ መርጦታል፡፡በመሆኑም ህዳር 20/2006 ዓ.ም ይህን አስመልክቶ የውል ስምምነቱ ላይ  የሀገረ ስብከት ተወካዮች፤የካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤና ልማት ኮሚቴ እንዲሁም የኤ.ቢ.ኤም. ኮንስትራክሽን ተወካይ በተገኙበት የውል ስምምነቱ ተፈርሟል፡፡

ሥራው በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚያልቅ ሲሆን ከፎካው ጋር ተያያዥ ያላቸው ሥራዎች ከላይ በተጠቀሰው የገንዘብ መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ይደረጋል፡፡ ኤ.ቢ.ኤም.  ኮንስትራክሽን ከ7,024,235.18  ብር ላይ 24,235.18 ብር በመቀነስ በ7,000,000 ብር ብቻ እንደሚሠራ ተስምምቷል የውሉ አካል እንዲሆንም ተደርጓል፡፡

የዕለቱ መርሃ ግብርም በክቡር ቆሞስ ሊቀ ሥልጣናት አባ ኪሮስ ፀጋዬ የካቴድራሉ ዋና አስዳዳሪ በፀሎት ተዘግቷል፡፡

{flike}{plusone}

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/0050.jpg 480 640 tc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png tc2013-12-01 08:12:482013-12-01 08:12:48የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ዘመናዊ ሁለ ገብ የመቃብር ፎካ ለመስራት የውል ስምምነት ተፈረመ

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓለ በሰላም አደረሰን አደሳችሁ! Link to: እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓለ በሰላም አደረሰን አደሳችሁ! እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓለ... Link to: የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳደር ጽ/ቤት በካቴድራሉ ግቢ ውጥ በአ/አ ሀ/ስብከት መዋቅራዊ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር ጥናት ላይ በመቃውሞ ድብቅ ስብሰባ ተካሂዷል ተብሉ የተዘገበውን በፅኑ ተቃወመ Link to: የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳደር ጽ/ቤት በካቴድራሉ ግቢ ውጥ በአ/አ ሀ/ስብከት መዋቅራዊ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር ጥናት ላይ በመቃውሞ ድብቅ ስብሰባ ተካሂዷል ተብሉ የተዘገበውን በፅኑ ተቃወመ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳደር...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top