የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳደር ጽ/ቤት በካቴድራሉ ግቢ ውጥ በአ/አ ሀ/ስብከት መዋቅራዊ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር ጥናት ላይ በመቃውሞ ድብቅ ስብሰባ ተካሂዷል ተብሉ የተዘገበውን በፅኑ ተቃወመ
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስደናቂ ከሚባሉ ታሪካዊ ቦታዎች አንዱ ነው፡፡ ካቴድራሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ዓለም ዓቀፋዊ ይዘት ያለውና አንጋፋ ካቴድራል ሲሆን ከታሪካዊነቱም በተጨማሪ፡-
• ዓለም አቀፋዊ የኃይማኖት ስብሰባዎች የሚካሄድበት፣
• የፓትርያሪኮችና የብፁአን ለቃነ ጳጳሳት በዓለ ሲመት የሚከናወንበት፣
• ብሔራዊ የመታሰቢያ በዓላትና ሥርዓተ ፀሎት የሚካሄድበት ነው፡፡
ከ6ቱ ቅዱሳን ፓትርያሪኮች መካከል 4ቱ የካቴድረሉ አገልጋዮችና የሥራ ኃላፊዎች የነበሩ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት የካትድራሉ አስተዳዳሪዎችና አገልጋዮች የነበሩ ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ይህም ካቴድራሉ ምን ያህል ትልቅ ቦታ እንደሆነና በቦታውም የሚመደቡ ሰዎች ምን ያህል ሊቃወንት እና የልማት አባቶች እንደሆኑ ግልፅ ነው ፡፡
ይሁንና ግን የታላቁና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሂዶ ቤተ ክርስቲያን መኩሪያና መመከያ የሆነውን ካቴድራል ስም ለማጥፋት December 14, 2013 ሐራ ዘተዋሕዶ በሚባል ብሎግ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳደር ጽ/ቤት በካቴድራሉ ግቢ ውጥ በአ/አ ሀ/ስብከት የመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር ጥናት ላይ በመቃውሞ ድብቅ ስብሰባ ተካሂዷል ተብሎ መዘገቡ እጀግ በጣም የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ከእውነት የራቀ ውሸት መሆኑን የካትድራሉ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡የብሎጉ አዘጋጆቹም ከእንዲህ አይነት ከእውነት የራቀ የአልቧልታ ሥራ እንዲታቀቡ በእግዚብሔር ስም ጠይቋል፡፡ካቴድራሉ አዲሱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መዋቅራዊ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር ጥናት ከየትኛውም ደብር /ካቴድራል ቀድሞ ሀገረ ስብከቱ ለሚያስተዳድራቸው ገደማትና አድባራት በተለይም የመልካም አስተዳደር ችግር ላለባቸው አንዳንድ ገደማትና አድባራት ትክክለኛና ወቅታዊ መሆኑን ቀድሞ የተረዳ መሆኑን ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብሏል፡፡
አጠቃላይ የካቴድራሉ የአሠራር ሂደት አሁን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከተዘጋጀው መዋቅራዊ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር ጥናት ቀደም ብሎ ከዓመታት በፊት በሥራ የተረጎመና አስከአሁንም ድረስ በዚሁ የአሠራር ሂደት እንደቀጠለ ነው፡፡ለዚሁም ነው ካቴድራሉ ልማታዊ ካቴድራል ሊሆን የቻለው፡፡በአሁኑ ሰዓት ካትድራሉ በተለምዶ 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ47ሚሊዮን ዘመናዊ በለ5 ፎቅ ሁለ ገብ ህንፃ እያስገነባ ሲሆን እንደዚሁም በካቴድራሉ አከባቢ በ7,000,000 ሁለ ገብ የመቃብር ፎካ በመገንባት ላይ ነው፡፡
በመሆኑም ታሪካዊና ልማታዊ የሆነውን የካቴድራሉን ስሙን ለማጥፈት ብሎም የጀመረውን የልማት እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ መሆኑን ሁሉም የቤተ ክርስቲኒቱ አባቶች፤ሊቃውንት፤አገልጋዮችና ምዕመናን እንዲገነዘቡልን እንፈልጋለን በማለት አሳስቧል፡፡
{flike}{plusone}