በመንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ካቴድራል የካህናት ሙያ ማሻሻያ ሥልጠና ተካሄደ

1551

የካቴድራሉ ስብከተ ወንጌል ክፍል ከካቴድራሉ ሰ/ጉ/አስተዳደር ጋር በመሆን ቀደም ብሎ በያዘው ዕቅድ መሠረት ከየከታቲት 1 ቀን ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት ያህል
• በትምህርተ ሃይማኖት
• በመጽሐፍ ቅዱስ
• በትምህርተ ኖሎት
• ስለቤተ ክርስቲያን አስተዳደር
• ስለ ስብከት ዘዴ አቀራረብ በተመለከተ ከ32 በላይ ለሆኑ መደበኛ ካህናት ሥልጠናው የተሰጠ ሲሆን ሠልጣኞቹ በሥልጠናው ያገኙት ግንዛቤ እራሳቸውን በሁሉም ሙያ በማብቃት መልካም የሆነ ክህነታዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ትልቅ ሥራ መሠራቱን እራሳቸው በአንደበታቸው መስክረዋል፡፡
ስብከተ ወንጌል ክፍሉ በዕቅድ ከያዘው አንዱ ይህ ሥልጠና በመሆኑ የመጀመሪያውን ዙር በእስፖንሰር ድጋፍ ያከናወነ ሲሆን ቀጣይ ሁለተኛና ሦስኛውን ዙሮች እንደግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በቀጣይ ጊዜያት ለመሥራት የዝግጅት ሥራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በመጀመሪያው ዙር ያሰለጠናቸውንም ካህናት በ22/6/08 የቤ/ካ አባቶች በተገኙበት አስመርቋል፡፡ {flike}{plusone}