በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ 6ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ

March 4, 2019
ቅዱሱሳን ፓትርያርኮቻችን በበዓሉ ላይ ተገኝተው በዓሉን ሲያከብሩ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፬ኛ ፓትርያርክ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ ከ34 በላይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የእስልምና ዋና ሐላፊ ሸክ አህመድ፣ የቤተክህነት ሠራቶኞች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በርከት ያሉ ምእመናንና እንግዶች በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በደማቅ መልኩ የ6ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በዓል ተከብሯል። በዕለቱ  የመርካቶ ቅዱስ ራጉኤል ሊቃውንት “ብፅዕት ከርስ እንተፆረተከ፣ ወብፁዓት አጥባት እንተኃጸናከ፣ ወበእንተዝ ቅዱስ ማትያስ ፓትርያርክ አብያተ ክርስቲያናት አፍቀራከ…እያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ ሲያቀርቡ፣ የሰንበት ት/ት ቤት መዘምራንም  “ ብፁዕ ወቅዱስ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጸሎትከ ትኩነነ… የሚል መዝሙር አቅርበዋል።

በመቀጠልም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣በክልል ትግራይ ደቡባዊ ዞን ማይጨውና ደቡባዊ ምሥራቅ ትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በዓሉን አስመክተው ንግግር አድርገዋል። ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ እንኳን ለዚህች 6ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በሰላም አደረሶት በማለት፣ ከሁሉም ቀድማ የነበረች ቤተክርስቲያናችን፣ የራስዋ ጳጳስና ፓትርያርክ ባልነበረባት ጊዜ በትግል ቆይታ እነሆ በእግዚአብሔር ፈቃድ በራሷ ጳጳሳት መተዳደር ከጀመረች ከአምሳ ዓመታት በላይ አስቆጥራለች። በቅርቡ የተደረገው የእርቅና የአንድነት ጉባኤም  ደስ የሚያሰኝ ነው፤  አሁንም አጠናክረን በመቀጠል ቤተክርስቲያናችን በአንድነትና በፍቅር መያዝ አለብን ብለዋል።

ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት በዓሉን በበዓሉ ላይ ተገኝተው በዓሉን ሲያከብሩ

በመጨረሻም፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ጋብዥነት፣ የካህናት አለቃ የምእመናን ወዳጅ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚህ በዓል ያደረሰን ከሁሉ በፊት እርሱ ይክበር ይመስገን ብለው እናንተም እዚህ የተገኛችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ብለዋል። በዛም ሰፋ ያለ አጥንትን ሰርስሮ የሚገባ ት/ት ሰጥተዋል፤ በተለይም የቤተክርስቲያን የወደፊት ዓላማ ምን መሆንና ምን መምሰል እንዳለባት፤ ወደኋላ መለስ ብለን አይተን፣ አሁን የት እንዳለን ተገንዝበን ለወደፊት ምን መሥራት እንዳለብን ራእይን የሚያሰንቅ  መልእክት አስተላልፈዋል።  ፍልሰተ ምእመናን አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑ ላይ ያተኮረው ንግግራቸው፣ ክስተቱን ለመቀልበስ ቅዱስ ሲኖዶስ መሠረታዊ የሆነ የአስተዳደር፣ የሐዋርያዊ ተልኮ መርሐ ግብር፣ የፋይናንስና የንብረት አያያዝ ሲስተም ዘርግቶ፣ የሰው ኃይል አስተዳደር አዘምኖ፣ሙሉ የምእመናን ጥያቄ የሚመልስ መሠረታዊ  የመልካም አስተዳደር ለውጥ ለማምጣት በቆራጥነት መሥራት አለበት። ይህንም የመሰለ ለውጥ እውን ለማድረግም የቤተክርድቲያኒቱን ምሁራን በሚገባ ማሳተፍና መጠቀም አለበት። የሃይማኖታቸው ፍቅር እንደ እሳት እያቃጠላቸው ስሕተቶች እንዲታረሙ ሐሳብና አስተያየት ለሚያቀርቡ፣ ቤተክርስቲያንን እንርዳ እናግዝ፣ እናገልግል የሚሉት ምሁራንና ሊቃውንትም ገንቢ ሐሳባቸውንና ዕውቀታቸውን ተቀብለን እናስተናግዳቸው ካሉ በኋላ በዚህ መንፈስ መግባባት ከተፈጠረ እየበዙ የመጡ ጩኸቶች ወደ ዝማሬ የማንለውጥበት ምክንያት አይኖርም በማለት አባታዊ ምክራቸውናን ለየት ያለ የወደፊቱ ራእያቸውን የሚያንጸባርቅ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/3.jpg 425 640 htc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png htc2019-03-04 10:01:092019-03-04 10:07:11የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ 6ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት ወቅታዊ ሁኔታዎችን አስመልክቶ ወቅታዊ አቋም አወጣ Link to: የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት ወቅታዊ ሁኔታዎችን አስመልክቶ ወቅታዊ አቋም አወጣ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰንበት... Link to: በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ሰንበት ትምህርት ቤት ምልአተ ጉባኤ ተካሄደ Link to: በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ሰንበት ትምህርት ቤት ምልአተ ጉባኤ ተካሄደ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ሰንበት ትምህርት...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top