በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ሰንበት ትምህርት ቤት ምልአተ ጉባኤ ተካሄደ

March 10, 2019

የካቲት 23 ቀን 2011 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት መካከል የፍቅር አገልግሎት እንዲዳብር ለመወያየት ታስቦ ምልአ ተጉባኤ ተካሂዷል፡፡

አስደናቂውና ታሪካዊው የካቴድራሉ ሕንፃ (ፍቶ ፋይል)

ጉባኤው የተጠራበት ዓላማ በተሰጣቸው እውቀት፣ ጊዜና ገንዘብ ውብና ማራኪ የሆነ አገልግሎት እያበረከቱ ያሉ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላትን አንድነት አስጠብቆ የነበረውና ያለውን አገልግሎት አጠናክሮ ለማስቀጠል ነው፡፡

በጉባኤው ከመንበረ ፓትርያርክ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና ከሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤቱ የተላኩ ደብዳቤዎች ተነበው የሰንበት ትምህርት ቤቱ ወቅታዊ ሁኔታ ከተብራራ በኋላ  በተቀመጠው የውይይት መርሃ ግብር መሰረት፡-

ምልአተ ጉባኤው በስፋትና በጥልቀት ከተወያየ በኋላ ሰንበት ትምህርት ቤቱ በዘመናት ብዙ ፈተናዎችን ተወጥቶ ብዙ ውጣውረዶችን አልፎ አሁን ያለበት ደረጃ የደረሰ፣ ብዙ ባለ ትሩፋት አባላትን ያፈራ እና የራሱ የሆኑ አወንታዊ መገለጫ ባሕርያት ያለው ቀዳማዊ  ሰንበት መሆኑ ተገልጾ  የሚከተሉት የመፍትሔ ሃሳቦች በጋራ ተቀምጠዋል፡፡

  1. አገልግሎት ድርድር የማያስፈልገው  የሰንበት ትምህርት ቤታችን መንፈሳዊ ግዴታ ስለሆነ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣
  2. ከማደራጃ መምሪያው እና ከካቴድራሉ በመጡ ደብዳቤዎች ላይ ምልዓተ ጉባኤው መስማቱ እንዳለ  ሆኖ  በጊዜአዊ አመራሩ በኩል ጥያቄ ከሚያነሱ ወንድሞች ጋር  ውይይት እንዲያደረግ፣
  3. ለብዙ ዘመናት  የዳበረው የእርስ በርስ ግንኙነት በወቅታዊ ሁኔታዎች መሸርሸር ስለሌለበት የነበረውን እና ያለውን የእርስ በርስ ግንኙነት አጠናክሮ ማስቀጠል ተገቢ ነውና ጊዜያዊ አመራሩ የእርስ በርስ ግንኙነት  ላይ ጠንከር ያለ ሥራ ቢሠራ፣
  4. ቃለ ዓዋዲው ስለሰንበት  ትምህርት ቤትእንቅስቃሴ ምን እንደሚል ተብራርቶ አማራጭ በሆነው የማስተማርያ መንገድ ትምህርት ቢሰጥ የሚሉ ነበር፡፡
የካቴድራሌ ሰንበት ት/ቤት በአገልግሎት ላይ (ፍቶ ፋይል)

በአጠቃላይ ውይይቱ የተያዘለትን ዓላማ እና ግብ የመታ እና የብዙሃኑን ሃሳብ የሰበሰበ፣ በአካል ያልተገኙ በተለይም ከሀገር ውጭ ያሉ አባላት ደስታቸውን እና ገንቢ አስተያታቸውን የሰጡበት እና አባላቱ ለአገልግሎት ያላቸውን ተቆርቋሪነት ያሳዩበት ነበር፡፡

ልዑል እግዚአብሔር ሰንበት ትምህርት ቤታችን እና አባላቱን ሁሉ በዘለዓለማዊ አባትነቱ፣ በማያልቅ ቸርነቱ እና በመለኮታዊ ጥበቃው ይጠብቅልን፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/sunday-school-11.jpg 427 640 htc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png htc2019-03-10 08:05:042019-03-10 08:05:06በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ሰንበት ትምህርት ቤት ምልአተ ጉባኤ ተካሄደ

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ 6ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ Link to: የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ 6ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ... Link to: ቃለ ዓዋዲው ስለሰንበት ትምህርት ቤት አደረጃጀት ምን ይላል? Link to: ቃለ ዓዋዲው ስለሰንበት ትምህርት ቤት አደረጃጀት ምን ይላል? ቃለ ዓዋዲው ስለሰንበት ትምህርት ቤት አደረጃጀት...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top