በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን ለ4ኛ ጊዜ እረዳታ ተሰጠ

                                            በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

10

ከአሁን በፊት በዌብሳይታችን አማካኝነት ወጣት ብሩክ አስራት ከዛሬ 4 ወር በፊት ጀምሮ ለካቴድራሉ አረጋውያን የሚሆን በየወሩ ለአረጋውያኑ የሚያስፈልጋቸውን የምግብ እርዳታ እየደረገላቸው መሆኑን ስንዘግብ መቆየታችን የሚታወስ ሲሆን አሁንም እንደተለመደው ለ4ኛ ጊዜ የ1 የወር አስቤዛ ሰጥቷል፡፡

25 ሌትር ጋዝ፤

15 ሌትር ዘይት 15 ኪሎ ስኳር፤

15 ኪሎ በርበሬ፤

15 ኪሎ ሽሮ፤

5 ፓኬት ሻይ ቅጠል

5 ኪሎ ጨው፤ እና 20 ሰሙና በእነ ወ/ሮ ማርታ ወርቄ፤በወንድሙ፤በወጣት ዳዊት መስፍን እና በጓደኞቹ አማካኝነት እርዳታውን የላከ ሲሆን ከ2 ሳምንት በፊት በወ/ሮ ማርታ ወረቄ፤በወ/ሮ ሮማን እሸቴ፤በወ/ሮ የምስራች አበበና በወጣት ዳግማዊ መስፍን አማካኝነት የአረጋውያኑ መኖሪያ ቤት የሆነውን የንግስት ዘውዲቱ መታሰቢያ ቤት አንድ ቀን ማጽዳታቸው ይታወቀል፡፡

አሁንም ከአገር ቤት ተመልሶ ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ቀደም ሲል ቃል በገባው መሰረት 4ኛ ጊዜ ለአንድ ወር የሚሆን የወር አስቤዛ በወንደሙና በጓደኞቹ አማካኝነት እርዳታ ሰጥቷል፡፡

በዚሁ ዕለት በክቡር ሊቀ ሥልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ አማካኝነት ለወጣት ብሩክ አስራት ቤተሰዎችና ለጓደኞቹ ጸሎትና ምስጋና እንዲሁም ቃለ ምእዳን ተሰጥተዋል ክቡር ሊቀ ሥልጣናት ኣባ ገ/ሥላሴ በላይ እንደገለፁት እንደ እነዚህ የመሰለ አቅመ ደካማ የሆኑ አረጋውያን መርዳትበእግዚአብሔር ዘንድ ወጋው እጅግ በጣም ትልቅ መሆኑን ገልፀው በተለይም በካቴድራሉ ቅፅረ ግቢ በንግስት ዘውዲቱ መታሰቢያ ቤት ተጠልለው የሚኖሩ አረጋውያን 24 ሰዓት እግዚአብሔር ሲለምኑ የመኖሩና እግዚአብሔር በሰዎች ላይ አድሮ የዕለት ጉርስ ከሚሰጥዋቸው ምዕመናን ውጭ ምንም ዓይነት ረዳት እንደሌላቸውና በአንዲት ጠባብ ቤት እስከ 8 የሚሆኑ አረጋውያን እናቶች ተጨናንቀው እንደሚኖሩና የምግብ ችግር ብቻ ሳይሆን የመፀዳጃ፤የማዕድ ቤት፤ የውሀና የንጽህና ችግርም እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ ፡፡በመጨረሻም በወጣት ብሩክ አስራት እየተደረገ ላለው ነገር ሁሉ ምስጋናቸው እጅግ የላቀ መሆኑን ገልፀው ሌሎችም የዚሁ የተቀደሰ ዓላማ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡