ዓመታዊው የዓጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ በዓል በድምቀት ተከበረ
በየዓመቱ ሐምሌ 7 ቀን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሚከበረው ዓመታዊው የሥላሴ በዓል በዚህ ዓመትም በመንበረ ጸባዖት ቅድሰት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኩሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት እጅግ በጣም ደማቅ በሆነ ሁኔታ በዓሉ ተከብሮ ውልዋል፡፡
በዚሁ ዕለት አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ በአብርሃም ቤት ተገኝተው ቤቱን የባረኩበት፣ የአንድነታቸውንና ሶስትነታቸው ሚስጢር የተገለፀበት ታላቅ በዓል ነው። በዓሉ መከበር የጀመረው ከዋዜማው ከሐምሌ6 ጀምሮ ሲሆን የካቴድራሉ ካህናትና መዘምራን ከዋዜማው ከቀኑ 3 ሰዓት ጀምሮ ለ30 ሰዓታት ያህል ሌሊትና ቀኑን ሙሉ ያለ ማቋረጥ ስብሃተ እግዚአብሔር ሲያቀርቡ ውለው አድረዋል፡፡
ይህመንፈሳዊ አገልግሎት ማለትም ስርዓተማህሌተ፣ ስርዓተቅዳሴ እንዲሁም ሰዓታትና ሰርክ ፀሎት በአጠቃለይ የስርዓተ አምልኮ አፈፃፀም በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ልዩ በመሆኑ የእምነቱ ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም እጀግ በጣም የሚስደንቅ በዓል ነው፡፡
በሌላ ዜና የካቴድራሉ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ሰርቲፊኬት ሐምሌ 6/2005 ዓ.ም የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ በተገኙበት መርሃ ግብሩ ተካሂዷል፡፡ በዚሁ ዕለት ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎችና ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተማሪዎች በካቴድራሉ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ ሽልማት ተሰጧቸዋል፡፡
{flike}{plusone}