በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
  • ቀዳሚ ገጽ
  • መ/ጸ/ቅ/ሥ/ካቴድራል
    • የአስተዳዳሪው መልእክት
    • ታሪክ
    • አስተዳደራዊ መዋቅር
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • ፎቶዎች
  • ቤተ መዘክር
    • የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር
    • ፎቶዎች
  • ት/ ቤት
    • መግቢያ
    • መሰናዶ እና 2ኛ ደረጃ
    • 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • 1ኛ ድረጃ ት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ
    • ፎቶዎች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • መግቢያ
    • አውደ ወራዙት
    • ፎቶዎች
  • አገልግሎቶች
    • መግቢያ
    • ፎቶዎች
  • ስብከተ ወንጌል
    • መግቢያ
    • ታሪክ
    • ፎቶዎች
  • Menu Menu

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖ 2ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ተከበረ

March 5, 2015

0019

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 2ኛ ዓመት የፕትርክና በዓለ ሲመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የካቲት 24 ቀን 2007 ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የሃይማኖት መሪዎች፤ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፤ አምባሳደሮች፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፤ የድርጅት ኃላፊዎች፤ የኮሌጅ ኃላፊዎች፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፤ ሠራተኞች፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ካህናት፤ ምዕመናንና ምዕመናት በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከብሯል፡፡
ቅዱስነታቸው በበዓሉ ላይ በሰጡት ቃለ ምእዳን “የእግዚአብሔር መንግሥት ማእከል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ጌታችን በሐዋርያት እንድትጠበቅ አድርጓል፡፡ ሐዋርያትም በበኩላቸው በተኳቸው ጳጳሳት እና ቀሳውስት ጠባቂነት ቤተ ክርስቲያን እንድትመራና እንድትጠበቅ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያዊት፤ አንዲትና ቅድስት እንደመሆኗ መጠን ከመጀመሪያው አንስቶ መንፈሳዊውን ጥበቃ በጳጳሳትና በቀሳውስት ስታከናውን ኖራለች፡፡ አሁንም እያከናወነች ነው፤ ወደፊትም በዚሁ ትቀጥላለች” ብለዋል፡፡
ቅዱስነታቸው አያይዘውም ጳጳሳትና ቀሳውስት የተሰጣቸውን የጠባቂነት ሚና አስመልክቶም “ይሁንና በዘመናችን እየተነሳ ያለው መሠረታዊ ጥያቄ የእግዚአብሔር መንግሥት ተጠሪ የሆኑት ጠባቂዎች ሓላፊነታቸውን በሚፈለገው ሁኔታ እየተወጡ ነው ወይ? የሚለው ጥያቄ በአሁኑ ጊዜ ዓለም አቀፋዊና የወቅቱ ጥያቄ ሆኖ ይገኛል፡፡ የእግዚአብሔር መንጋ የሆኑት ክርስቲያኖችን በባሕር ማእበል ሞገድ እንደሚናጥ መርከብ በጥርጣሬ እየተናጡ አጉል መንገድ ላይ እንዲቀሩ እያደረገ ነው፡፡ ከመንጋው ተነጥሎ እንደሚቅበዘበዝ በግ ባለማመን ማእበል እያንጓለሉት ነው፡፡ በጠባቂነት የተሾምን ሁሉ ከተጠያቂነት ለመዳን በዛሬው እለት የበዓለ ሲመተ ክህነትን ለማክበርና ማሰብ በተሰባሰብንበት ቀን የመንጋ ጥበቃ ሥራችን የት ላይ እንዳለ ማሰላሰል አለብን፡፡ መንጋው እየበዛ ነው ወይስ እየቀነሰ፤ ጤናማ ነው ወይስ በሽተኛ? የሚለውን ጥያቄ አንስተን ተጨባጭ መልስ ልንሰጥ ይገባል” በማለት ተናግረዋል፡፡
ከተወቃሽነት ለመዳን መደረግ ስለሚገባው አገልግሎት ሲገልጹም “የተመረጥንበት የጥበቃ ሓላፊነት በትክክል ካልሰራንበት በመንጋውም፤ በታሪክም፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በእግዚአብሔር ፊት ወቀሳ እንደማይቀርልን ተገንዝበን ከተጠያቂነትና ከተወቃሽነት ለመዳን የጥበቃ ሥራችንን በርትተን መሥራት ይገባናል፡፡ የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ ተብለናልና” ብለዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የወላይታ ኮንታ ደውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በበኩላቸው 56ኛውን በዓለ ሲመተ ፕትርክና እና 2ኛውን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዓለ ሲመተ ፕትርክናን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልእክት “እግዚአብሔር ለቅዱሳን ያለው ፍቅር በርቀት የሚመዘንና የሚለካ አይደለም፡፡ እነሱ በአጠገቡ ሆነው የእሱን ሥራዎች እንዲሠሩ ፈቅዶላቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት በምድር ላይ መጋቢዎች፤ እንዲሁም አስታራቂዎች አድርጓቸዋል፡፡ “ለአባቶቻችን ያዘዘውን ለሚመጣው ትውልድ ለልጆቻቸው ያስታውቋቸውም ዘንድ አልሰወሩም” እንዲል ቅዱስ ዳዊት ዛሬ በዚህ ዐውደ ምሕረት ላይ እንደምንመለከተው ቅዱስነትዎ ከአባቶችዎ የተረከቡትን ሓላፊነት በታማኝነት ለመጠበቅ ቃል የገቡበትን እለት ለማስታወስ ነው” ብለዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከት ወንጌል መምሪያ የበላይ ጠባቂና የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  በቅዱስ ፓትርያሪኩ ትምህርት እንዲሰጡ የተጋበዙ ሲሆን ቅኔውንና ትምህርቱን አዋህደውና አዋዝተው ሰማዕያኑን እጅግ በአስደነቀ መልኩ አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፤ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፤ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተው የበዓሉ ፍፃሜ ሁኗል።
{flike}{plusone}

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/0019.jpg 480 640 tc https://eotc-htc.org/a/wp-content/uploads/logo_am2.png tc2015-03-05 16:13:362015-03-05 16:13:36የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖ 2ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ተከበረ

መፈለጊያ

Search Search

በቅርብ የተለቀቁ

  • የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የንግሥ በዓል በመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ በድምቀት ተከበረ። 
  • ⛪️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተቀነጨበ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የካቴድራሉ እድሳት የሚገኝበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። (መስከረም 2017 ዓ.ም)
  • ከእዚህ በላይ ደስታ ምን አለ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፤
  • “ቤተ መቅድሳችንን እናድስ ለቀጣዩም ትውልድ እናድርስ ፣ ኃላፊነታችንንም እንወጣ!” መሪ ቃል
  • ሁላችንም የኢትዮዽያ ልጆች ከከተማ እስከ ገጠር ያለን የመ/ጸ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጠባቂዎች እና ደጋፊዎች ነን‼️
  • ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ህንጻ ዕድሳትን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ፤
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፕትርክና የካቲት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከበራል።
  • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት

አስተያየቶች

    © Holy Trinity Cathedral | Website by atbiya.com
      Link to: በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የአንድነት ጉባኤ መርሃ ግብር ተካሄደ Link to: በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የአንድነት ጉባኤ መርሃ ግብር ተካሄደ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የአንድነት... Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2007 ዓ.ም. የትንሣኤ በዓልን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2007 ዓ.ም. የትንሣኤ በዓልን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ...
      Scroll to top Scroll to top Scroll to top