ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተቀፀል ጽጌ እና በእድሳት ምክንያት ወርዶ የነበረው መስቀል የማስቀመጥ ሥነሥርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

d

የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ.የ6ኛው ፓትርያርክ በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ

                            በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ ብፁእ አቡነ ማትያስ በእስራኤል የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ስድስተኛው የኢትዮጵዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ፓትሪያሪክ በመሆን የካቲት 21/2005 ዓ.ም እንደተመረጡ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በዚሁ በተካሄደው የድምፅ አሰጣጥ 806 ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ አቡነ ማትያስ 500 ድምፅ በማግኘት ነበር ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው የተመረጡት፡፡ በዚሁም መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ […]

b

ሰበር ዜና

ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢትየጽያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ስድስተኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመረጡ፡፡ ከ806 ድምጽ 500 ውን በማግኘት ፓትርያርክ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ መሠረት ብፁዕ አቡነ ማትያስ 500 ድምፅ በማግኘት 1ኛ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ 98 ድምፅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 98 ድምፅ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በ70 ድምፅ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ 39 ድምፅ በዚህም መሠረት […]

7

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን 6ኛውን የፓትሪያርክ ምርጫ የካቲት 21/2005 ዓ.ም እንደምታካሂድ አስታወቀች፡፡

                                በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ ድስተኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ለማስመረጥ የተቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ ከምርጫው ሂደት ጋርና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ በተመለከተ ዛሬ ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም ለጋዜጠኞች ወቅታዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በዚሁም መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን 6ኛ የፓትሪያሪክ ምርጫ ለማካሄድ ቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነው መሠረት ከሊቃነ ዻዻሳት ፣ከጠቅላይ ቤተክህነት ሰራተኞች ከአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ከሰንበት […]

10

በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን ለ4ኛ ጊዜ እረዳታ ተሰጠ

                                            በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ ከአሁን በፊት በዌብሳይታችን አማካኝነት ወጣት ብሩክ አስራት ከዛሬ 4 ወር በፊት ጀምሮ ለካቴድራሉ አረጋውያን የሚሆን በየወሩ ለአረጋውያኑ የሚያስፈልጋቸውን የምግብ እርዳታ እየደረገላቸው መሆኑን ስንዘግብ መቆየታችን የሚታወስ ሲሆን አሁንም እንደተለመደው ለ4ኛ ጊዜ የ1 የወር አስቤዛ ሰጥቷል፡፡ 25 ሌትር ጋዝ፤ 15 ሌትር ዘይት 15 ኪሎ ስኳር፤ 15 ኪሎ በርበሬ፤ 15 ኪሎ ሽሮ፤ 5 ፓኬት […]

6

የ2005ዓ.ም የጥምቀት በዓል በድምቀት ተከበረ

እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥመቀት በሰላም በጤና በሕይወት አደረሳችሁ፡፡

                                  በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

6

በየዓመቱ ጥር 10 እና 11 የሚከበረው የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥመቀት በገነተ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን መሪነት ከ13 ታቦታት በላይ በሚያድሩበት በጃን ሜዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤልና ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ በዓሉ ተከብሮ ውልዋል፡፡ የዓመቱ ተረኛ የሆነው የገነተ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን መዘምራን ዕለቱን በማስመልከት ያሬዳዊ ዝማሬ

‹‹ ተሰሃልከ እግዚኦ ምደረከ ሃሌ ሉያ ወረደ ወልድ እም ሰማያት ውስተ ምጥማቃት በፍስሐ ወበሰላም››በማለት ያሬዳዊ ዜማ አቅርበዋል፡፡ በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ዐበይት በዓላት ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል የጥምቀት በዓል አንዱ ነው፡፡ይህም በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ፤ በማእከለ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በየዓመቱ ከዋዜማው ከጥር 10 ጀምሮ በደመቀ ሁኔታ በማክበር ላይ ትገኛለች፡፡ ለእኛ አብነት ይሆነን ዘንድ፤ የእዳ ደብዳቤያችንን እንደ ገል ቀጥቅጦ እንደ ሰም አቅልጦ በደላችንን ይደመስስ ዘንድ ጌታ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይህንን መሠረት በማረድግ በየአብያተ ክርስቲያናቱ የሚገኙ ታቦታት በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ በካህናትና ዲያቆናት፤ እንዲሁም በሰንበት ት/ቤቶች መዘምራንና ምዕመናን በዝማሬ በመታጀብ በአቅራቢያቸው ወደሚገኘው ታቦት ማደሪያ በማምራት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በመሔድ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ማምራቱን ያበስራሉ፡፡ ‹‹ያን ጊዜም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ናዝሬት መጣ ዮሐንስም በዮርዳኖሰ ወንዝ አጠመቀው›› እንዲል፡፡/ማቴ.3፡1/ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መስራቿን መድኅነ ዓለም ክርስቶስን ለዓለም የምትሰብክበት፣ ከእርሱም ያገኘችውን፣ ይህም ዓለም እንደሚሰጠው ያልሆነውን፣ የእግዚአብሔር ልጅነት፣ ሰላም፣ ፍቅርና ትሕትና ለዓለሙ ትሰብክበታለች፡፡ እንዲሁም ለሀገራችን በጎ ገጽታን በመፍጠር ረገድ ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ ጎብኚዎች ተደንቀው የሚያዩትና በመስተንግዶው የሚደመሙበት በመሆኑ ሃይማኖታዊ በዓሉን በልዩ ትኩረት ታከብራለች፡፡

ዋዋጎ ቱውፊታዊ ድራማ

ይህ ቲያትር ሙሉ ገቢው ለካቴድራሉ እድሳት ስለሆነ ሁሉም ሰው ሼር ያድርገው፡፡ በተጠቀሱት ቀናትም ይህንን በአይነቱ ለየት ያለውን ትውፊታዊ ቲያትር በመመልከት እውቀትዎን ያሳድጉ፡፡

በቅርብ የተለቀቁ

donation

አስተያየትዎን ይጻፉልን

Click here to add your own text

Click here to add your own text