ስልክ፡ 011-1-23-35-18 / 011-1-23-35-15
Click here to add your own text
Click here to add your own text
ይህ ቲያትር ሙሉ ገቢው ለካቴድራሉ እድሳት ስለሆነ ሁሉም ሰው ሼር ያድርገው፡፡ በተጠቀሱት ቀናትም ይህንን በአይነቱ ለየት ያለውን ትውፊታዊ ቲያትር በመመልከት እውቀትዎን ያሳድጉ፡፡
Click here to add your own text
Click here to add your own text
በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን ለ2ኛ ጊዜ የምግብ እህል እረዳታ ተሰጠ
የዛሬ ሁለት ሣምንት አካባቢ ወጣት ብሩክ አስራት ከአሜሪካን አገር መጥቶ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በንግስት ዘውዲቱ መታሰቢያ ቤት ተጠልለው ለሚኖሩ 15 አረጋወያን በአካል ተገኝቶ የአረጋውያኑ የአኗኗር ሁኔታ እንደጎበኘና ለጊዜው የሚስፈልጋቸውን ልዩ ልዩ የአንድ ወር የምግብ አስቤዛ እርዳታ እንዳደረገላቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡ አሁንም ከአገር ቤት ተመልሶ ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ቀደም ሲል ቃል […]
በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን እረዳታ ተሰጠ
በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ “ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፡፡” መዝ. 40¸1 “እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ”2ኛ ቆሮ. 9¸7 እርዳታውን የሰጠው በአሜሪካን አገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊው ወጣት ብሩክ አስራት ነው፡፡ወጣት ብሩክ አስራት አረጋውያኑ የሚኖሩበት የንግስት ዘውዲቱ መታሰቢያ ቤት ተገኝቶ የአረጋውያኑ የአኗኗር ሁኔታ የጎበኘ/የተመለከተ ሲሆን በየሳምነቱ ሰኞ፤ረቡዕና ዓርብ በካቴድራሉ በኩል ለእያንዳንዳቸው 2 እንጀራ እንደሚሰጣቸውና ለዙሁም […]
በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሠራተኞች የአስተዳደርና የቅርስ አያያዝ ስልጠና ተሰጠ
በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ መስከረም 18/01/05 ይህ ስልጠና የተዘጋጀው በካቴድራሉ አስተዳደር ጽ/ቤት አማካኝነት ሲሆን ለዚሁ ስልጠና እንዲሰጡ የተጋበዙ ምሁራን አሰልጣኞች፡- 1ኛ. ዶ/ር አባ ኃለማርያም መለሰ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን 2ኛ. መ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ የቅርሳቅርስና ቤተመዘክር ኃላፊ ሲሆኑ በተቀመጠላቸው መርሃ ግብር መሠረት በተሠጣቸው ርዕስ ስልጠናውን/ትምህርቱን በሚገባ ሰጥተዋል/አስተምረዋል የአስተዳደርና የቤተ ክርስቲያን አገልገሎት በተመለከተ […]
የጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሥርዓተ ቀብር በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፀመ
ነሐሴ 27ቀን 2004 ዓ.ም
በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቀብር ስነስርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ነሐሴ 27 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ተፈጽሟል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩን የቀብር ስነ ስርዓት በተመለከተ ከንጋቱ 11 ሰዓት በታለቁ ቤተ መንግስት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ስራአስከያጅ፣6 የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ካህናት ጋር በህብረት ሙሉ ፀሎተ ፍትሐት አድርሰዋል በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ከ15/2004 ዓ.ም መሐራ እግዚኦ ለነፍሰ መራሔ መንግሥትን ገ/ማርያም፤ አቤቱ የመራሔ መንግሥታችን የገብረ ማርያምን ነፍስ ማር” በማለት ጸሎትዋን አድርሳለች በማድረስ ላይም ትገኛለች፡፡በተለይም በ26/2004 ለ27 አጥቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከ600 በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ካህናትና መዘምራን በህብረት ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ሙሉ ሌሊቱን ፀሎተ ፍትሐት ሲያደርሱ አድረዋል፡፡
በታላቁ ቤተ መንግስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመከላከያና የፖሊስ አባላት፣ ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡
በመስቀል አደባባይም ከ25 በላይ የሀገራት መሪዎችና ርዕሳነ ብሔራት እንዲሁም በርካታ የአህጉራዊና አለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች፣ የመከላከያና ፌደራል ፖሊስ ሰራዊት፣ የመንግስት ሰራተኞችና እንግዶች አስከሬኑን ለመቀበል በስፍራው ተገኝተዋል፡፡
ክብርት ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን እንዳሉት መለስን ከልጅነቱ ጀምሮ ነው የማወቀው፡፡ ዱሮም ጀምሮ ህልሙ የነበረው በኢትዮጵያ ፍትህ፣ ሰላምና እድገትን ማስመዝገብ ነበር፡፡ ሁሌም ያልም የነበረው ድህነትን ስለመታገል ነበር፡፡ ጊዜውን ሁሉ ይሰጥ የነበረው ህልሙን ለማሳካት ነበር፡፡ ልጆቼም የሚፈልገውን ጊዜ አልነፈጉትም፡፡ መለስ ለፍትህ፣ ለሰላምና ለፍቅር የቆመ ነበር፡፡ ይህንንም የኢትዮጵያ ህዝብ በማረጋገጡ በጣም አመሰግናለሁ ፡፡
እኔም ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ሆኜ እሱ የጀመራቸውን የልማት ተግባራት ለማስቀጠል የበኩሌን አስተዋፅኦ አበረክታለሁ ብለዋል፡፡
8 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስከሬን ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የደረሰ ሲሆን፡፡ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራልም ለ30 ደቂቃ ያህል ደውል የተደወለ ሲሆን አስከሬኑም ከሰረገላው ወርዶ ወደተዘጋጀለት ልዩ የፀሎት ቦታ አርፏል፡፡ በካቴድራሉ ካህናትና መዘምራንም ስርዓተ ፀሎት ተካሂዷል፡፡
ከ9 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ላይ የፀሎት ስነ ስርዓት እንደተፈፀመ አስከሬኑ ቤተ ክርስቲያኑን በቀኝ በመዞር 9 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስከሬን ወደተዘጋጀለት የቀብር ቦታ ያረፈ ሲሆን፤የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀብር ስነ ስርዓት መጠናቀቁን በማስመልከት 21 ግዜ መድፍ ተተኩሷል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አጭር የህይወት ታሪክ
የብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ
ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ የብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝደንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ሥርዓተ ቀብራቸው ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም እኩለ ቀን ላይ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ከፍተኛ […]